ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የመንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ ተገለጸ (2)

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሚያዝያ 9/2010..እንደምታወቀው በየአመት ረመዳን ወር ሳይገባ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ለቀናት የሚዘልቅ የጋራ ምክክር መድረክ ይካሄዳል።በመሆኑም ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የክልሉ መንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በፋፈን ዞን በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ መንግስት አስታውቀዋል።

በተጠማሪም ጉባኤው በአውበሬ ከተማ 3ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከግንቦት አንድ እስከ ግንቦት 3/2010ዓም የሚዘልቅ ከመሆኑ ባሻገር ከረመዳን ወር 3ቀናት ያህል እንደምቀድምም ታውቀዋል። የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ አስተናጋጁ ከተማ አውበሬን ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።