የኢ.ሶ.ክ.መ. የዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የ9 ወራት እቅድ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በጅግጅጋ ተጀመረ

ጅግጅጋ(cakaaranews)አርብ፤ሚያዝያ 19/2010ዓም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2010ዓም እቅድ የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬ እለት በጅግጅጋ ከተማ በክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ከሊ2 መሰብሰብያ አደራሽ ተጀመረ።

በጉባኤው የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በ2010ዓም የታቀዱት የልማት፤የሰላምና መልካም አስተዳደር ስራዎች አስመልክቶ በ9 ወራቱ የተከናወኑት የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ በግምገማው  የሚተኮር ሲሆን መድረኩን በጋራ የመሩት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲመሀሙድ፤የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤና የኢሶህዴፓ የድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ እንዲሁም የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋራህ ናቸው።የመድረኩ መረጃዎች በቀጣዩ ዘገባዎቻችን በሰፊው የሚንተነትን ይሆናሉ።