በደጋህቡር ከተማ አስተዳደር እየተገባ ያለው ድልድይ በማፋጠን ላይ እንደሚገኝ የቸረር ዞን አስተዳዳሪ አስታወቀ

ደጋህቡር(Cakaaranews)ሀሙስ፤ግንቦት 16/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ህዝብ ለዘመናት መሠናክል ሆነውበት የቆዩትን የሃገር ውስጥ ፀረ-ሠላም ሃይሎች እንደ ኡቦ (ኦብነግ) ፣ አልኢትሃድ ፣ አልሸባብ እና የመሳሰሉትን በሃገር መከላኪያና በክልሉ ልዩ ኃይል አማካኝነት ካስወገደ ወዲህ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የክልሉ መንግሥትም ሆነ መሪው ድርጀት ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ የፀጥታን ጉዳይ ከአረጋገጡ በኋላ  ወደ መሠረተ ልማት ግንባታዎች መግባታቸው ይታወሳል። ከእነዚህም መካከል ት/ቤቶች ፣ የዉሃ መሠረተ ልማት ፣ የህዝብና የእንሰሳ ጤና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ፣ የመንገድና ትላልቅ ድልድዮች ግንባታዎች በሰፊው ለማከናወን እንደተሠማራና ይህንንም ማረጋገጡን እና የመሠረተ ልማቱን ግንባታ እያስቀጠለ እንዳለ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ወቅት የክልሉን ህዝብ ፍላጎት ለማርካትና እንዲሁም የማህበረሠቡን የመሠረተ ልማት ፍላጎት ችግሮችን ለመቅረፍ ዘላቂ መፍትሄዎችን ለማምጣትት በርካታ የዉሃና የመንገድ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። ከእነዚህም መካከል የደጋህቡር ከተማ መስተዳደርን የሚያቋርጠው ትልቁ የጀረር ወንዝ በከተማው የሚገኙትን አራት ዋና ዋና ቀበሌዎችን እንዲያገናኝ ሆኖ የድልድይ ግንባታው እየተፋጠነ መሆኑን የደጋህቡር ከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በተጨማሪም የድልድዩ ግንባታ በጥሩ ሁኔታ እየተናወና እንደሚገኝም የጀረር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሙሁመድ ሀሰን ሱፊ ገልጿል፡፡ “ይህ ድልድይ የ8 ሜትር ስፋት ያለው ፣ የ27 ሜትር እርዝመት እና ቁመቱ 7 ሜትር ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅም በክረምት ወቅት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ሲያቆራርጥ የነበረውም ጎርፍ መፍትሄ እንደሚያገኝ ማረጋገጥ እንችላለን” ብለዋል አስተዳዳሪው ።

በሌላ በኩል በደጋህቡር ከተማ  ነዋሪዎች የማህበረሠብ ክፍሎች በበኩላቸው በደጋህቡር እየተገነባ ባለው ድልድይ የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ የዚህ ድልድይ ግንባታ የክልሉ መንግሥት ለህብረሰቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚያደርገውን ያላሰለሰ ጥረት ከመንግሥት ጎን በመሆን በርብርብ እንደሚያጠናቅቁም ገልፀዋል።