በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ ሃገር በቀልና ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት አቀረቡ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)አረብ፤ሰኔ 15/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዓመት ሁለት ጊዜ በሚያዘጋጀው የጋራ መድረክ ሃገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶችዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ግምገማ መካሄዱ ተገለፀ።

በተጨማሪም የክልሉ የውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዲ መሀመድ  የጋራ መድረኩን አስመልክተው የሰጡት  ግብረመልሲ "የዛሬው ስብሰባ አላማ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመንግሥት ድርሻን ሳያካትት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሃገር በቀል እና ዓለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ከዕቅድ ጀምሮ ከክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በመተባበር  የድጋፍ በመሥራት ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜ ከ20 በላይ የሚሆኑ ሃገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች በክልላችን የልማት ሥራዎች እያከናወኑ ይገኛሉ በመሆኑም በጋራ መድረኩ ላይ በእነዚህ ድርጅቶች የተከወኑ የልማት ሥራዎች ሪፖርት ከማቅረባቸው በተጨማሪም የተከወኑ የልማት ሥራዎች በተግባር እና ተጨባጭነት ባለው አግባብ ይገመገማል። በዚህ አካሄድ እንደሚታወቀው የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እንደመሆኑም ጭምር በእነዚህ የበጎ አድረጎት ድርጅቶች የተሠሩ ሥራዎች መመዘኛ ይደረገባቸዋል በእኛ በኩልም ከጋራ መደረኩ ቀደም ብሎ የተከወኑ ሥራዎችን አስመልክቶ ቁጥጥር እና ክትትል በሚያደርጉ ባለሞያዎቻችን ከወረዳ እስከ ቀበሌ እንዲታዩ  በማድረግ በመድረኩ እያንዳንዱ የበጎ አድራጎት ድርጅት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ውይይትም ይደረግበታል" ሲሉ ገልጿል።

በሌላ በኩል በክልሉ እየተከናወነ ያለው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን እና የጋራ ፖሮግራሞች አተገባበርን በመፈተሽ ቀጣይ አቅጣጫ ለማሰቀመጥ እንደሚጠቅምም የመድረኩ ተሳታፊዎችና ባላድርሻ አካላቱ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ ሃገር በቀልም ሆነ ዓለም አቀፍ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች የሠው ሃይላቸውን በሚያደራጁ ጊዜ ለክልሉ ተወላጆችና ለሃገር ውስጥ ባላሙያዎች  ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸውም አቶ አህመድ አብዲ አሳስበዋል።