የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ዛሬ በአዲስ አበበ የደረሠውን የቦምብ ጥቃት እንደሚያወግዝ በከባድ አቋም ገልጿል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ16/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢሶህዴፓ)የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአዲስ አበበ በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ የቦምብ ፍንዳታ ያቀነባበሩትን፣ የፈጸሙትን እና ከዚህ አስጸያፊ አስነዋሪና ድርጊት በስተጀርባ ያሉትን ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነት የማይወዱና የሀገራችንን ህዝቦች ለመበታተን፣ ለማፋጀት እንዲሁም ሊያባሉን የፈለጉ የአሸባሪዎች ድርጊት ነው ሲሉ መላው የክልሉ ህዝብና መንግሥት በከባድ አቋማቸው ማውገዛቸውን ገልፀዋል።

በመቀጠልም የኢሶህዴፓ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ለተጎዱ ወገኖቻችን እና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ መራራ ሃዘን እየገለፀ አስጸያፊ ድርግቱን በከባድ አቋም እንደሚያወግዝ ይገልፃል።