በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተገኛውን ድፍድፍ ነዳጅ በይፋ ተመረቀ

ኢለሌ(cakaaranews)ሀሙስ᎓ሰኔ 21/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያሶማሌክልል ህዝብና መላው የሀገሪቷ ዜጎች በክልሉ ውስጥ የሚገኙ  እምቅ የፈጥሮ ሀብቶቻቸውን በተለይ በቀዳሚነት ለበርካታ የክልሉ አከባቢዎች የታደለው የተፈጥሮ ጋዝ᎓ፔትሮልየም እና ሌሎች የሀገሪቱ ማዕድናትም በአግባቡ ለመጠቀም  ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የሚሆን ጊዜ በጉጉት ሲጠበቁ የነበረውን የፔትሮልየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በኢትዮጵያሶማሌክልል ፕሬዝዳንትክቡርአቶአብዲመሀሙድ ፤በኢፈዴሪ ማዕድን ᎓ፔትሮልየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መለስ አለሙና በኢፈዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በኢለሌ ወረዳ የተገኙት 6 የፔትሮልየምና ተፈጥሮ ጋዝ ጉድጓዶች መካከል ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሶስት የድፍድፍነዳጅ(cruel-oil)ጉድጓዶች  በዛሬው እለት በጋራ ተመርቀዋል።ይህ የድፍድፍነዳጅ ጉድጓዶች በቀን 800 በርሚል ነዳጅ የማምረት አቅም እንዳላቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም በተለያዩ ሀገራት እንደ ራሺያ᎓አውስተሬሊያ᎓አሜሪካ᎓ኢንግሊዝና መሌዠያ ድርጅቶች በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ  አከባቢዋች የተለያዩ ነዳጅ ፈለጋ ጥናቶች ብያደርጉም ሳይሳከላቸው ቀርተዋል። ነገር ግን  የክልሉ መንግሥት የክልሉ ብሎም የሀገሪቱን ነዳጅ ሀብት ለማውጣትና የሀገሪቱ ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ በወሰደውን እልህ አስጨራሽ ጥረትና በጉዳዩ ላይ በተሰጠው አቅምና እውቀት መሰረት ከ4 አመታት በፊት ከቻይናው የፖሊ ጂሲ ኤል (Poly-GCL) ድርጅት ጋር በኢትዮጵያሶማሌክልል በሚገኘውን የኦጋዴን ጋዝ ቁፈራ እንድያካሄድ ከስምምነት መድረሱን ይታወሳል።የፖሊ ጂሲ ኤል ባላሙያዎችም በአከባቢው በሚገኙ ሁሉም የነዳጅ አይነቶች አመርቂ ውጤቶች አስገኝተዋል።

በሌላ በኩል በሸቤሌ ዞን ኢለሌ ወረዳ የተገኘው የነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያሶማሌክልል ፕሬዝዳንትክቡርአቶአብዲመሀሙድ  ኡመር᎓የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች᎓የፖሊ ጂሲ ኤል ፔትሮልየም ድርጅት አመራር አካላት᎓አምስቱ የሀገር መከላኪያ እዞች ዋና አዛዠ ጄኔራሎች᎓በኢትዮጵያ የቻይና አምቤሲ አመራር አባላት᎓ሃገር ሽማግሎች᎓የክልሉ ዲያስፖራ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደገላቸው እንግዶችም ተገኝተዋል።በተመሳሳይም በነገው እለት ጄህዲን/ካሉብ የተገኙ የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮልየም ጉድጓዶችም በኢትዮ-ሶማሌክልል ፕሬዝዳንት እና በፌዴራል የስራ ሃላፊዎች እንደምመረቁም ተገልጸዋል።

በዚህም በዛሬው የነዳጅ ምርቃት መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ.ሶ.ክ.ፕሬዝዳንትክቡርአቶአብዲመሀሙድ "እስካአሁን ድረስ ምንም አይነት ችግር ሳይፈጠር ሠራተኛው እና ድርጅቱ በሠላም የፕሮጀክቱን ሥራ በማጠናቀቁ በመጀመሪያ ለአላህ ምስጋና እናቀርባለን። በመቀጠል ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ፣ ለሀገርመከላከያ ሠራዊትና ለክልሉ ፀጥታ ሃይሎች ብሎም ለፌዴራል መንግሥትና ለፖሊ ጂ.ሲ.ኤል ፔትሮሊየም ካምፓኒ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ነገር ግን አሁንም የክልሉ ህዝብ እና መንግሥት እስከ ፕሮጀክቱ ፍፃሜ ድርስ ቀን ከተሌሊት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሁሉም የባለድርሻ አካላት በፌዴራልም ሆነ በክልልም ህዝቡም ተባብረን ድህነትን ታሪክ እናድርገው" ብሏል።

ፕሬዝዳንቱ ዛሬ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ህዝብ አዲስ ምዕራፍ እንደተከፈተ ገልጾ በዛሬው እለት የኢለሌ ተፈጥሮ ነዳጅ በማስመረቃቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ከመግለጻቸው ባሻገር ኢለሌ ወረዳ ለሀገሪቱ ህዝብ የሥራ ፈጣሪ እድል እንድትሆን በመመኘት ኢለሌ የክልሉና የሀገሪቱ ልማት መነሻ ትሆን ዘንድም መርቋል።

በተያያዜም የኢፈዴሪ የማዕድን᎓ፔትሮልየምና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴ ሚኒስትር አቶ መለስ አለሙ ባቀረቡት ንግግር "በዛሬው እለት የኢለሌ ድፍድፍ ነዳጅ በረገጥናት የእናት ሃገራችን ከርሰ ምድር ወይም ደግሞ ፅንሰ ምድር ወደ አንድ ምዕተ ዓመት የተጠጋ ዘመን ሲፈለግ የነበረው ድፍድፍ ነዳጅ በዘመን ቀመር የዛሬዋ ዕለት የሃገራችን ምድር የመካንነት ጊዜ አብቅቶ የእርግዝና ምልክት የሚታይበት ታሪካዊ ቀን በመሆኗ እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን ለማለት እወዳለሁ" ተናግረዋል።አያይዞም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥትና ህዝብ እንድሁም ለክልሉ ጸጥታ አካላት ለፖሮጀክቱ ያደረጉትአስተዋፅኦሚኒስትሩ የላቀ ምስገና አቅርቧል።

የድፍድፍ ነዳጅ ሀብቱ ሀገሪቱ አሁን ከገባችበት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለማውጣት የምታደርገው ጥረት ለማገዝ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውና ነዳጁ ከኤክስፖርት ፋይዳ ባሻገር ለሀገር ውስጥ እንዱስተሪዎች እንደሚውል እንደሁም በቅርቡ የድፍነዳጅ ፓይፕ ዝርጋታ ሥራዎች እንደሚጠናቀቁም የኢፈዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ አስረድቷል።

በመጨረሻም በቆራሄይ ዞን ዶበወይን ወረዳ ጄህዲን ወይንም በካሉብ ፐተገኙ የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮልየም ጉድጓዶች በነገ እለት በኢትዮጵያ ሶማሌክልል ፕሬዝዳንት እና በፌዴራል የስራ ሃላፊዎች እንደምመረቁም ተገልጸዋል።