የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ ሲያስተማራቸው የነበሩትን 3900 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ23/2010ዓ.ም  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና የሚገኘው የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በርቀት እንዲሁም በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሲያስተምራቸው የነበሩትን 3900 ተማሪዎች ማስመረቁ ተገልጿል።

ሃገሪቷ ከያዘቻቸው የሚሊኒየም ግቦች መካከል ዜጎችን በትምህርት ዕውቀት ማብቃት አንዱ ሲሆን በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው ጅግጅጋ የሚገኘው ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ በመደበኛ፣ በተከታተይ እና በርቀት በተጨማሪም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም ሲያስተምራቸው የነበሩትን 3900 ተማሪዎች በዛሬው እለት ማስመረቁ ተገልጿል።

የምርቃት ሥነ-ሰርዓቱ  በብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ም/ፕረዝዳንትና የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋራህ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ባለፉት 10 ዓመታት በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች  የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋፋቱና በሁሉም የመሠረተ ልማት መስኮች አመርቂ ሥራዎችን መስራታቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ አርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር ዘርፎች አቅም የሚያሳደጉና ውጤታማ የሆኑ በርካታ የጥናትና ምርምር ተግባራትን መስራቱንና በአርብቶ አደር እና ከፊል አርሶ አደር ጥናትና ምርምር ሥራዎች በሀገሪቷ ካሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በቀዳሚነት እንደምትገኝም ም/ርዕሰ መስተዳደሯ አብራርተዋል።

በተመሳሳይም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልአዚዝ ኢብራህም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2010ዓም ለ10ኛ ጊዜ በአንደኛ እና በ2ተኛ ዲግሪ በመደበኛነት የተመረቁት ተማሪዎች ብዛት 1346 ሲሆኑ በዘንድሮ በተከታታይ መርሃ ግብር የተመረቁ ተማሪዎች ብዛትም 2691 መሆናቸውንና በርቀት እና በሌሎች ፖሮግራሞችም ዩኒቨርሲትው 4037 ተማሪዎችን አስመርቋል ብለዋል።

በተጨማሪም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ10 አመታት ውስጥ 27, 738 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮችና በተለያዩ መርሃግብሮች ማስመረቃቸውንም ዶ/ር አብዱልአዚዝ ኢብራህም ገልጿል።

በሌላ በኩል ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለ10ኛ ጊዜ ካስመረቃቸው ተመራቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ እና በማዕረግ ለተመረቁት  ተማሪዎችን የተለያዩ የሜዳሊያና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ለሁለት ግለሰቦችም የክብር ዶክትሬት መስጠቱም ተገልጿል።

በመጨረሻም ተመራቂ ተማሪዎች ከበርካታ ውጣ ውረዶች በኋላ ዛሬ ለዚህ ምርቃት በማብቃታቻውን እጅግ መደሰተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በቀጣይም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል።