በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳደግ የሞያ ስልጠና መሰጠት መጀመሩ ተገለፀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤ሰኔ 25/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት በክልሉ ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳደግ የሚረዳ የሞያ ስልጠና መሰጠት መጀመሩ ተገልጿል። ስልጠናው ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በትምህርቱ ዙሪያ የሚሠሩ ባለሞያዎች፣ አመራሮች እና የዴስክ ሠራተኞች እየተሳተፉ እንደሆነም የክልሉ ትምህርት ቢሮ  አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳደግ ከ93 ወረዳዎችና 6 የከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ባለሞያዎች ስልጠናው መሰጠት መጀመሩ ተገልጿል።በዚህም ለ10 ቀናት የሚቆይ መሆኑን  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራህም አደን ገልፀው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት "ስልጠናው በሁሉም ወረዳዎች የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሳደግ ታስቦ ነው የተዘጋጀው። ይህንንም በእቅድ ላይ የተመሠረተ ሞያዊ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል። እናንተም ስልጠና በመከታተልና ወደመጣችሁበት ስትመለሱ በትምህርቱ ዙሪያ ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ መሥራት ይኖርባችኋል” ብሏል።

በተጨማሪም በትምህርት ዙሪያ የሚሠሩ ባለሞያዎችና አመራሮች የሞያ ብቃታቸውን ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት ተከትሎ በክልሉ የተማሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መሆኑንም  የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገልፀዋል።

ይህን ስልጠና ከ93 ወረዳዎች እና 6 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የትምህርት ባለሞያዎች፣ አመራሮች እና የትምህርት ክትትል ሠራተኞች እንዲከታተሉት መደረጉም ተገልጿል። ለ10 ቀናት የሚቆየው ይሄው ስልጠና በትምህርት አመራር እቅድ እና ክትትል እንዲሁም በሌሎች ሞያዊ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግም ቢሮ ኃላፊው ገልጿል።

በተጨማሪም በክልሉ ትምህርት ቢሮ የመምህራን ልማት ዳይረክተር አቶ አብዲሃኪም መሀመድ አሊ "በመጀመሪያየተማረ ትውልድን ለማፍራት የሚቻለው መምህራንን እና አመራሮችን በሞያው እውቀታቸውን ሲያሳድጉ መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ”በማለትገልፀዋል።።

 በመሆኑም  ይህ ለ10 ቀናት የሚወስደው ስልጠና ከዚህ ቀደም የነበሩ ድክመቶችን ለመቅረፍና  ባላሙያዎቹ ከስልጠና ልምድ በመቅሰም እነሱም ይህንኑ ወደታች በማውረድ ለ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተያዘው እቅድ ውስጥ በመተግበርና ትምህርት ቤቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል መድረክ ከመሆኑ በላይ የርዕሰ መምህራንን እና ሱፐር ቫይዘሮች አቅም በማሳደግ ተማሪዎች በእውቀት ለማብቃት የሚረዳ ስልጠና መሆኑንም ዳይረክተሩ አስገንዝቧል።