በስዊድን የሚኖሩ የኢ.ሶ.ክ.ዲያስፖራ ኮሙኒቲ በክልሉ የተመዘገበውን ዘርፈ ብዙ ለዉጥ የሚደገፉበት ደማቅ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ማክሰኞ፤ሰኔ 03/11/2010 ዓ.ም  በስዊድን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የአፍዴር ዞን ተወላጅ የሆኑ የዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላት በክልሉ እየታየ ያለውን ሁለንተናዊ ለዉጥ በመደገፍ ብሎም ለማስቀጠል፣ ለማበረታታትና ከክልሉ መንግሥት ጎን መሆናቸው የሚያሳዩበት ደማቅ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ።

በተጨማሪም ለበርካታ ዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ድፍድፍ ነዳጅ በኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልልበማዉጣቱ በጣም እንዳስደሰታቸዉና ድፍድፍ ነዳጁ ለሃገሪቱም ሆነ ለክልሉ ፈጣኝ እድገት እንደሚያመጣና የዘመናት ህልማቸውን እንዳረጋገጠም ገልጸዋል።

በዲያስፖራ ኮሙኒቲው የድጋፍ ሥነስርዓት ላይ መልዕክታቸውን በስልክ ያስተላለፉት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ማስተባበሪ ቢሮ ሃላፊና በፕሬዝዳንቱ ቅርታ ማስተናጃ ዘርፍ አማካሪ አቶ አብዲረዛቅ ሰሃኔ በመጀመሪያ ምስጋናቸውን በማቅረብ፤ በመላዉ ዓለም ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላት ክልሉ እያስመዘገባቸው ያሉ ዘርፈ ብዙ ለውጦች እንደ ፀጥታ፣ መልካም አስተዳደር እንዲሁም የተገኙትን ድሎች ለማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

ባለፈው ሳምንት ሥራውን በይፋ የጀማረው የኢለሌ ድፍድፍ ነዳጅ መውጣትን ተከትሎ የክልሉ ዲያስፖራ ኮሙኒቲዎች አድናቆታቸውን እየገለፁ እንደሚገኙና በዚህም በርካታ የሥራ ዕድሎች መፍጠር እንደሚቻልም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ሥም ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

በመጨረሻም በስዊድን ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የዲያስፖራ ኮሙኒቲ እና በስካንዲኒቪያ ጥላ ሥር ለሚገኙ የዲያስፖራ ኮሙኒቲ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ፣ ለሃገር ዕድገትም እንዲሠሩ ጥሪ አቅርቧል።