በሶማሊያ የተ.መ.ድ.የስደተኞች ጉዳይ ልዩ መልዕክተኛ በጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

ጅግጅጋ (cakaaranews)ሩቡ᎓ሐምሌ 04/2010ዓ.ም.ሃገራችን ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበልና በማስተናገድ ከአፍሪካ ቀንድ ሃገሮች በግንባር ቀደም ትጠቀሳለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃገራችን ከሚገኙት ክልሎች መካከል የኢ.ሶ.ክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ተቀብሎ  በተለያዩ መጠሊያ ጣቢያዎችን እያስተናገደ ይገኛል።

በዚህም በተ.መ.ድ የሶማሊያ ስደተኞች ጉዳይ ልዩ መልክተኛ አቶ መሀሙድ አብዲ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል ዓለምአቀፍ አየርማረፊያ ሲደርሱ የኢ.ሶ.ክ ት/ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አደም እና በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የለጋሽ ድርጅቶች እና ስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ አብዲበሪ መአሊን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተያያዜም ልዩ መልዕክተኛው በአየር ማረፊያውእንግዳ ማረፊያ በነበራቸዉ አጭር ቆይታ "እኔ በዋናነት ወደ እዚህ የመጣሁትበት ጉዳይ በተ.መ.ድ እና በኢትዮጵያ በኩል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የሚኖሩትን የሶማሊያ ስደተኞች ለመጎብኘት ነው። እንደሚታወቀው ከ25 ዓመታት በላይ በእንግድነት የመጡትን እነዚህን የጎረቤት ሃገር ስደተኞች እንደሃገራቸው ከዛም በላይ እንደቤታቸው በእዚህ ሃገር ሲኖሩ በመቆየታቸውን የኢትዮጵያን መንግሥትና የክልሉን መንግሥት በእዚህ አጋጣሚ በጣም ለማመስገን እንወዳለን” በማለት ልዩ መልዕክተኛው ተናግረዋል።

 በተጨማሪም በጉብኝታቸውን ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ጋር በመተባበር ለስደተኞቹ የሚያስፈልጋቸው መሠረታዊ ድጋፎች፣ እገዛዎችና ግንባታዎች እንደሚወያዩ አቶ መሀሙድ አብዲ ገልጿል።

የኢ.ሶ.ክ ት/ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አደም በበኩላቸዉ "ልዩ መልዕክተኛው እዚህ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች  የሚገኙትን የሶማሊያ ስደተኞች እና የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን በመዟዟር የሚጎበኙ ይሆናል።  ከዚህ በተጨማሪም የስደተኞቹን ጉብኝት ካጠናቅቁ በኋላ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ሥራ ላይ ይሰማራሉ። ልዩ መልክተኛው ጉብኝት ከሚያደርጉባቸው ቦታዎች መካከል የዶሎ አዶ እና መልከዲዳ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ተጠቃሽ ናቸው። በቀጣይም የተለያዩ ሥራዎችን በጋራ የምንሠራ ይሆናል" ሲሉ  ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ልዩ መልዕክተኛው  የጉብኝታቸው ዋና አላማው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልም ሆነ የፌዴራሉ መንግሥት  የተለያዩ ዓለምአቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሶማሊያ ስደተኞች ለሚያደርጉት ድጋፍ ያላቸውን መልካም ግንኙነት ሀገራቸ ያላት ድጋፍ ለማሳየት ነው ብሏል።