የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ጎዴይ ቅርንጫፍ በርቀትና በተከታታይ ት/ት ፖሮግራም በተለያዩ ት/ት መስኮች ያስተማራቸው 434 ተማርዎች አስመረቀ

ጎዴይ(cakaaranews)አርብ፤ሐምሌ 13/2010 ዓ.ም በጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ጎዴይ ቅርንጫፍ በርቀትና በተከታታይ ት/ት ፖሮግራም በተለያዩ የት/ት መስኮች ሲከታተሉ የነበሩ  434 ተማርዎች በጎዴይ ካምፓስ ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት ዩኒቬርሲቲው በአከባቢያቸው ተጠቃሚ ለደረገላቸው የከፍተኛ ትምህርት እድል ደስተኛ መሆናቸው ገልጸዋል።

ጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ከተቋቋመበት ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱና በክልሉ የተማረ የሰው ህይል በማፍራት የተጠለበትን ሀገራዊ ግዴታቸው በኃለፈነት ለመውጣት ሰፊ እንቀስቀሴዎች ሲያደርግ መቆየቱን ይታወሳል።በዚህም ዩኒቬርሲቲው በተለያዩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልና አጎራባች አከባቢዎች የተለያዩ በርቀትና በተከታታይ  ትምሀርት መስጫ መዕከላትና ቅርንጫፎች በመክፈት የከፍተኛ ትምሀርት እድል በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆብ በጎዴይ ቅርንጫፍ በርቀትና በተከታታይ ት/ት ፖሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸው 434 ተማሪዎች አስመርቋል።

በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይም የጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ  ከፍተኛ አመራር አካላት፣መምህራን፣የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጎዴይ ቅርንጫፍ በአንደኛና ሁለተኛ ዲግሪ መርሃግብር ያስተማራቸው 434 ተማሪዎችን ለ9ኛ ጊዜ አስመርቋል። በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ለተመራቂ ተማሪዎችና ለተመራቂ ቤተሰቦች የእንኳን ደሳላችሁ መልዕክታቸው  ያስተላለፉት የዩኒቬርሲቲው አከዳሚክና ምርምር ም/ፕረዝዳንት አቶ ኢልየስ ኡመር  ዩኒቬርሲቲው በዛሬ በእለት በተለያዩ  ዲፓርቲመንቶች በአንደኛና ሁለተኛ ዲግሪ ት/ት መስኮች ለ9ኛ ጊዜ   ያስመረቃቸው ተመራቂዎች በክልሉ እየተካሄዴ ያለው የልማት ጉዞ  የድርሻቸውን አስተዋጸኦ እንዲያበረከቱ ጠይቋል።

በተመሳሳይም  በምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ በክቡር እንግድነት የተገኙ የቀብሪደሀር  ዩኒቬርሲቲ ም/ፕረዝዳንት አቶ መሀመድ መሀሙድ  ተመራቂዎቹ ለሀገርቱም ሆነ ለክልላቸው ህዝብ በተማሩበት ዘርፍ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም በሀገሪቱ እየተከናወነ ባለው ዘርፈ ብዙ የልማት ዘርፎች ለማስቀጠል የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡም ጥሪ አቅርበዋል ።

በመጨረሻም ተመራቂዎቹ በተደረገለቸው የምርቃት ዝግጅት እጅግ ደስተኛ መሆናቸው ገልጸው፣ጅግጅጋ ዩኒቬርሲቲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱና በኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልልም በመደበኛ በርቀትና በተከታታይ  የትምሀርት መርሃግብሮች ተማሪዎች በማስመረቅ በሀገራችን እድገት ላይ ከፍተኛ ድርሻ  አበርክተዋል ብለዋል።