የኢ.ሶ .ክ ሃገር ሽማግሌዎች በሀገር ውስጥና በወጭ ሀገራት ለሚገኙ የክልሉ ተወላጆች በሙሉ በጅግጅጋ ለሚካሄደው የሰላም ኮንፈሬንስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

ጅግጅጋ(cakaaranews)እሁድ፤ሐምሌ 15/2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሃገር ሽማግሌዎች፣ገራዶች፤ኡጋሶችና ሱልጣኖች፣ወበሮችና ሌሎች በክልሉ ህዝብ ዘንድ ክቡርና ተቀባይነት ያለቸው ጎሳ መሪዎች በዛሬው እለት በጅግጅጋ ከተማ በራሳቸው ተነሳኝነት በጋራ ያወጡት አቋም መግለጫ፤በሀገር ውስጥና በወጭ ሀገራት ለሚገኙ  የክልሉ ምሁራን፤ደጋፊዎች፣ተቋሚ ግለሰቦችና የፖለቲካ ተፎካካሪ ድርጅቶች አመራሮችና ወጣቶች፣ሴቶችና ሌሎች የክልሉ ማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም መላው የክልሉ ተወላጆች በሙሉ በቀጣይ ሐምሌ 28 ቀን፣2010ዓ.ም ወይንም እ.አ.አ በአጎስት 5/2018 በጅግጅጋ ከተማ ለሚካሄደው የሰላምና አንድነት ኮንፈሬንስ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በኮንፈረንሱ ላይም አልፎ አልፎ የሚታየው ልዩነቶች የሚወገድበትና ወደ መግባባት የሚሸጋገርበት የህዝብ ኮንፈረንስ ሲሆን ዋናነት በክልሉ ሰላም፣ልማትና በአንድነት ጉዳዮች የሚወያይበት ታላቅ ጉባኤ እንደሆነም ሃገር ግማግሌዎቹ ገልጸዋል።

በተጨማሪም በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ምሁራን፤የክልሉ መሪ ድርጅት ደጋፊዎች፣ተቋሚ ግለሰቦችና የፖለቲካ ተፎካካሪ ድርጅቶች አመራሮች፣ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች በክልሉ ህብረተሰብ ዘንድ ተሰሚነትና ተቀባይነት ያላቸው ግለሰቦችም እንደሚሳተፉ የሀገር ሽማግሎቹ ቃል አቀባይ የሆኑት ገራድ ኩልሚየ ጋራድ መሀሙድ አስታውቋል።

በመጨረሻም በቅርቡ ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ የተዘረዙት የኦብነግ(ኦጋዴን ብራዊ ነጻ ወጭ ግንባር)አባላት በሰላምና አንድነት ኮንፈራንሱ ላይ እንድገኙና ልክ እንደሌሎቹ ሃገራዊ የፖለቲካ ተፎካካሪ ድርጅቶች በሀገሪቱ ፖለቲካ፣ኢኮኖሚ፣ማህበራዊና ልማታዊ ጉዳዮችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም በሀገሪቱ በተፈጠረው ይቅርባይነት፣መከባበርና ሀገራዊ አንድነትን  እንዲደምሩ የሀገር ሽማግሎቹ ተወካይ ገራድ ኩልሚየ ጋራድ መሀሙድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።