የጅጅጋ ከተማ አስተዳደር በምግብ ዋስትናና ተጠቃሚነት ሲሰጥ የነበረው ስልጣና መጠናቀቁ ተገለፀ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ማክሰኞ፣ሐምሌ 17/2010. በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ኤጀንሲ ከጅግጅጋ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለአንድ ሳምንት ያልህ የምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ኤጀንሲ ባላሙያዎች እና የከተሞች ምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና መጠናቁ ታውቋል።

የስልጠናው አላማ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች  በከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም አካል የሆኑት የአካባቢ ጥበቃና ጽዳት፣ የከተሞች ውበትና ጽዳት እንዲሁም በከተማ ልማት መርሃ ግብር የህብተሰቡን ተሳትፎን ለማሳደግና የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በምግብ ዋስትና ራሳቸው እንዲችሉ የላቀ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ካሊድ አብዲራህማን  ገልፀዋል።

በተጨማሪም በስልጠናው ላይ ከተለያዩ የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ቀበሌዎች ለተወጣጡና አቅመ አናሳ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መካፈላቸውን በመግለጽ፣ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች በከተማው ሥራ እድል ፈጠራ፣ በአካባቢ ጥበቃና ጽዳት፣ በከተማ ልማት፣ በከተማ ውበትና ጽዳት እንዲሁም በምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ዘርፎች የተጠቃሚዎቹን  ተሳትፎ ለማሳደግና ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ እንደሆነም አቶ ካሊድ አብዲራህማን  ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ፕሮግራም 10ሺህ አቅመ አናሳ ግለሰቦችን ተጠቃሚ ያደገረ ፕሮግራም መሆኑንም በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የኢሶህዴፓ ፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ አብዱላሂ ሙሁመድ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የምግብ ዋስትናና ሥራ ፈጠራ ፕሮግራም የሃገሪቱ ዘላቂ ልማት መርሃ ግብር(SDG)አካል መሆኑን በጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር የሚኖሩ አቅመ አናሳ የማህበረሰብ ክፍሎች ኑሮ ትልቅ ለውጥ ያመጣ መሆኑንም ሃላፊው አቶ አብዱላሂ ሙሁመድ አብራርተዋል።

በመጨረሻም የስልጠናው ተካፋዮች ከስልጣናው ባገኙት እውቀትና ክህሎት እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽና ከስልጣናው የቀሰሙትን እውቀትና ልምድ ለከተማው ህብረተሰብ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ ሃገራችን ከዓለም ባንክ በከተሞች ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ዕቅድ ከታቀፉ 11 ከተሞች መካከል አንዷ ጅግጅጋ ስትሆን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ወደ 5,000 (አምስት ሺህ) የሚጠጉ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም የሥራ ሃላፊዎቹ ገልጸዋል።