በአፍዴር ዞን ቸረቲ ወረዳ በእርሻ ሥራ የተሰማሩ ማህበራት ጥሩ ምርት እያገኙ መሆኑ ተገለፀ

ቸረቲCakaaranews)አርብ፤ሐምሌ 20/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ አፍዴር ዞን ቸረቲ ወረዳ በዞኑ የሚገኘውን የዌብ ወንዝ በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ በወረዳው በርካታ የእርሻ ማህበራት የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ላይ ሲገኙ ውጤቱም ጥሩ እንደሆነ መናገራቸው የቸረቲ ወረዳ መስተዳደር ጽ/ቤት ገልጿል።

የዌብ  ወንዝ በአካባቢያቸው ከሚያልፋባቸውና ይዟቸው ከሚመጡ ትሩፋቶች ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የአፍዴር  ዞን ቸረቲ  ወረዳ ይጠቀሳል። ታዲያ የዚህን ወንዝ ጥቅምና የመሬቱ ትልቅ ዋጋና አጠቃቀም የገባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በመስኖ እርሻ ሥራ ማህበራት ተደራጅተው በአካባቢያቸው ከሚያልፈው ከዚሁ ወንዝ በመጥለፍ በርካቶች በእርሻ ምርቶቻቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን ጽ/ቤቱ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ይህ ያልተነካ ለም መሬት ለእርሻ ምቹ በመሆኑ እነዚህ ማህበራት እንደ ሽንኩርት፣ ሃብሃብ፣ ካሮትና ሌሎችም እያመረቱት ሲሆን አቶ በሺር ዲሪዬ ስለ እርሻ ሥራ ማህበሩ“በመጀመሪያ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ለሥራ ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት ካለ ምንም የሚያቅት ነገር የለም፤ ይህ አሁን ላይ መሬቱ በምርት ተሸፍኖ የምትመለከቱት ከዚህ ቀደም ምንም አይነት ሥራ ሳይሠራበት ታጥሮ የተቀመጠ ባዶ መሬት ነበረ። ያው እንደምታዩት እዚህ ለመድረስ እኔ በግሌ ብዙ ጥረት አድርጌያለሁ፤ የመንግሥት ግብርና ባለሞያዎችም ብዙ እገዛ አድርገውልኛል፤ ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ምርት ሰብስበናል የቸረቲ  ሽንኩርት በጣም ተፈላጊ ነው፤ በሚቀጥለው ደግሞ ሌላ አይነት ምርት ነው የምናመርትበት ፈጣሪ ይመስገን ጥሩ ውጤት እያገኘን ነው”ሲሉ ገልፀዋል።

በመጨረሻም አቶ በሽር ዲሪዬና የእርሻ ሥራ ማህበራቱ የክልሉ መንግሥት እያደረገላቸው የሚገኘው ድጋፍ እጅግ መልካም እንደሆነ ገልፀው ወደፊት የያዙትን የእርሻ ሥራ በማስፋትና በዘመናዊ የእርሻ መዳበሪያ ቁሳቁስ በመታገዝ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን እንደሚፈልጉም አስታውቀዋል።