በውጭ ሃገራት የሚኖሩ የኢ.ሶ.ክ ዲያስፖራዎች ክልሉ በሚያካሂደው የሰላምና አንድነት መድረክ ላይ ለመገኘት ወደ ክልሉ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል መደረጉ ተገለፀ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሐሙስ፤ሐምሌ 26/2010 ዓ.ም በአውሮፓና ስካንዲኒቪያን ሃገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ዲያስፖራ ማህበረሠብ አባላትና ሌሎችም የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በቅርቡ በክልሉ በሚካሄደው የሰላምና አንድነት የጋራ ምክክር መድረክ ላይ ለመገኘት ወደ ክልሉ ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ሲገቡ በክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተገለፀ።

እነዚህ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ባሳለፍነው ሳምንት የክልሉ ሃገር ሽማግሌዎች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃጋራት ለሚኖሩ መላው የክልሉ ተወላጆች ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት በሰላምና አንድነት የምክክር መድረኩ ላይ ለመገኘት የመጡ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በተለያዩ የአውሮፓ እንደ ዴንማርክ፣ጀርመን በመሳሰሉት ሃጋራት የሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሠቡ አባለቱን በመወከል ኡጋስ አብዲረሺድ ጃማእ ሙርሰል፤ በተጨማሪም በስካንዲኒቪያን ሃገራት የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራ ማህበረሠብ አባላት ዋና ሃላፊ አቶ አብዲኑር ቀልቢ መሀመድና አባለቱ ሲሆኑ ወደ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል ዓለምአቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ንግድ፣ትራንስፖርትና እንዱስተሪ ቢሮ ሃላፊ፣ የዶ/ር አብዱልመጅድ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲንና የክልሉ ሄጎ ወጣቶች ንቅናቄ አባላት ተወካይ ኤርፖርት በመገኘት ደማቅ አቀባበል ማድረጋቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም ዲያስፖራ አባላቱ በበኩላቸው በክልሉ ርዕሰ መዲና በጅግጅጋ በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እጅግ ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር፣የክልሉ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ያደረጉለት አቀባበል ከጠበቁት በላይ መሆኑንም ገልጸዋል።