እንኳን ደስላቹ እንኳን ደሳለን የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ የፈዴራል የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሠጡ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ፤ግንቦት 2 ቀን 2010.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ከፈተኛ አመራር አካላት የኢሶክመ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ በዛሬ እለት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይአህመድ በፈዴራል መንግስት መዋቅር ለሾሙት የኢሶህዴፓ አባላት የእንኳን ደስላቹ እንኳን ደሳለን መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።በዚህም በዛሬ እለት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፈዴራል  የስራ ሃላፊዎች ከሾሙት መካከል ወ/ሮ ሰሀርላ አብዱላሂ የኢፌዴሪ የህዝብተወካዮች ም/ቤት አባልና በጤና ዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ያላት ሲትሆን የኢፈዴሪ ጤና ጥበቃ ሚንስተር ዴታ ተደርጋ ተሾመዋል።በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትር ሚንስቴር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚንስተር ዴታ የነበችው ወ/ሮ ፈርሂያ መሀመድ የኢፈዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚንስቴሪ ሚንስተር ዴታ የተደረገች ሲሆን ወ/ሮ ኢፍራህ አሊ ሙሳ በነበረችው የሳይንስና ቴክኖለጂ ሚንስተር ዴታ በድጋሜ ተሾመዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት ለተሾሙት አዳዲስ ሚንስቴር ዴታዎች በገሀሪቱ አመራርነት ከፍተኛ ለውጥ እንዲያስገኙ ዘንድ የተመኘ ሲሆን የኢ.ሶ.ክ.መ.መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ለኢህአዴግ ማዕካለዊ ጽ/ቤትና ለኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ስም ዝርዝራቸው መላኩን ይታወሳል።

 በመጨራሻም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ አመራር አካላት የኢሶክመ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርን ጨምሮ ለኢህአዴግና ለኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢሶህዴፓ ጥያቀ በአግባቡ በመመለሳቸውን የላቀ ምስገና ያቀርበዋል።

 ለተሾሙት አዳዲስ ሚንስቴር ዴታዎችን የክልሉ መሪ ድርጅት ለኢሶህዴፓ ከፍ ያለ ምስገና ያቀርበዋል።  

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በጅግጅጋ ከተማ ሲያካሄድ የነበረው የተማሪዎች ዉድድርና ስምፖዝየም አጠናቀቀ

ጅግጅጋ (Cakaaranews) ሀሙስ፤ ሚያዚያ 25/2010ዓ.ም. የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር  ለጅግጅጋ ከተማ ተማሪዎች የፓናል ዉይይት እና ቃለ መጠይቅ መድረክ አዘጋጅተዋል።

በክልሉ ትምህርት ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች ዉድድር እና ፓናል ዉይይት በዛሬው ዕለት በዉድድሩ ፍፃሜ የተገናኙት የጅግጅጋ ሞዴል ስኩል ት/ቤት እና ጂግጂጋ መሰናዶ ት/ቤት  ተገኝተዋል። በዉድድሩ ማጠናቂያ መድረክ ላይም የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት ፤የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ᎓ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ተወካዮችና የተወዳዳሪ ት/ቤቶች ርዕሰ መምህራን ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ መዝጊያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀሙድ አህመድ ኑር “የዚህ ዓይነት መድረኮች ለታማሪዎች ያላቸው ሃገራዊ ፋይዳዎች የላቀ እንደሆነና ለወደፊትም  የተማሪዎች ዉድድር እና ስምፖዝየም ዉይይቶች በሌሎች ት/ቤቶች ላይ እንዲዳረሱ እንዲሁም የሀገራችን የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርትን ትኩረት እንደሚሰጠ ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት አቶ ኢልያስ ኡመር  ዉድድር መድረኩ ለታዳጊ ተማሪዎቻችንን ከፍተኛ ፋይዳ መኖሩንና ተማሪዎችን የሚያነቃቃና የእርስ በእርስ ፉክክርን የሚፈጥር ነው ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበር ተነሳሽነት የተዘጋጀ እንደሆነና መመስገን እንደሚገባቸውም ም/ፕረዜዳንቱተናግረዋል፡፡  ለወደፊትም ዩኒቨርሲቱ ለክልሉ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን በፍላጎታቸው በዩኒቨርሲቲው ተነሳሽነት እንደሚያመቻቹ  የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክና ምርምር ም/ፕረዜዳንት አቶ ኢልያስ ኡመር  ገልጿል፡፡

በመጨረሻም የዉድድሩ አሸናፊ የሆኑት በአንደኛነት የጂግጂጋ ሞዴል ስኩል ት/ቤት እና በሁለተኝነት  የጅግጅጋ መሰናዶ ት/ቤት ሲሆኑ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲና በክልሉ ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀላቸው ሽልማቶች ከዕለቱ ዕንግዳ ተበርክቶላቸዋል፡፡

 

 

የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህል ሳምንት በጅግጅጋ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዝያ 18/2010ዓም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባህል ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ በባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በክልሉ ርዕስመዲና በጅግጅጋ  ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ።በሥነ-ስርዓቱ ላይ ከ6ቱ ከተማ መስተዳደሮችና ከዞኖች የተወጣጡ ባህል ቡዱኖች በክልሉ ዋና ከተማ ጎዳናዎች በርካታ የሶማሌ ባህል ትርዕቶችና ባህላዊ ውዝዋዜዎችን በተለያዩ መንገዶች እያሳዩ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ፉኣድ አህመድ ጃማዓ እና የሳይንስና ቴክኖለጂ ም/ቢሮ ሃላፊና የቀድሞ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ባሼ አብዲ እስማኢል  በክልሉ ሚዲያ በጋራ ባነጋገሩት ወቅት የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሔረሰብ ባህላዊ ቅርሶች ለማስተዋወቅና ባህላዊ ትውፋቶች ወደ ቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ በክልል ደረጃ የባህል ሳምንት ፌስትፋል ማዘጋጀቱን ወሰኝ ሚና እንዳለው አስታውቀዋል።አያይዞም የክልሉ ባህል ሳምንት ፌስትፋል ዋና አላማ በክልሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙየማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ለማጥናት፤ለመንከባከብና ለማስተዋወቅ ከመሆኑ በተጨማሪ የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ መስተዳደሮች የሚገኙ ባህል ቡዱኖች ለማስተሳሰር እንደሆነም ሃላፊዎቹ ገልጿል።

 የከተማ መስተዳደሮችና ወረዳዎች የተወጣጡ ባህል ቡዱኖች በክልል ደረጃ የብሔረሰቡ ባህል ሳምንትማዘጋጀቱና የተለያዩ የክልሉ ባህል እሴቶች እራሳቸው ባህላዊ ቅርሶችን መለዋወጣቸው እና ባህላቸው በአደባባይ በትዕይንት ማቅረባቸው ደስተኛ መሆናቸውን ለሚዲያ ተናገረዋል።

በተጨማሪም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ በክልል ደረጃ የሚከበረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ባህል ሳምንት ለቀጣዩ ቀናት በክልሉ ሚዲና የተለያዩ የሶማሌ ባህላዊ ቅርሶች፤ባህላዊ ትርዕቶች በትላልቅ ጎዳናዎች እንደሚቀርቡና በፌስትፋሉ የሙዝየም ባህላዊ ቁሳቁሶችና የባህል ጥናታዊ ጽሁፎች በስምፖዝየም እንደምቀርቡና በጅግጅጋ ከተማ አከባቢዎች የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦች እንደሚገኙም የኢ.ሶ.ክ.መ.ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስረድቷል።

የኢ.ሶ.ክ.መ. የዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የ9 ወራት እቅድ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በጅግጅጋ ተጀመረ

ጅግጅጋ(cakaaranews)አርብ፤ሚያዝያ 19/2010ዓም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የ2010ዓም እቅድ የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬ እለት በጅግጅጋ ከተማ በክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ከሊ2 መሰብሰብያ አደራሽ ተጀመረ።

በጉባኤው የክልሉ ዞኖች፤ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በ2010ዓም የታቀዱት የልማት፤የሰላምና መልካም አስተዳደር ስራዎች አስመልክቶ በ9 ወራቱ የተከናወኑት የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ በግምገማው  የሚተኮር ሲሆን መድረኩን በጋራ የመሩት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲመሀሙድ፤የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤና የኢሶህዴፓ የድርጅት ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ እንዲሁም የክልሉ ም/ፕሬዝዳንትና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሱኣድ አህመድ ፋራህ ናቸው።የመድረኩ መረጃዎች በቀጣዩ ዘገባዎቻችን በሰፊው የሚንተነትን ይሆናሉ።

የኢ.ሶ.ክ. ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ወደ አሜርካ አቀኑ

አዲስ አበባ(Cakaaranews)ሀሙስ፤ሚያዝያ 18/2010ዓ.ም. በኢሶህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ከደር አብዲ ኢስማእል የሚመራ ከፍተኛ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድ ወደ ሀገረ አሜርካ በሯል፡፡ ከልዑኳን ቡዱኑ መካከል የኢ.ሶ.ክ.መ. የእንስሳትና ከፊል አርሶ አደር ጥናትና ምርምር ተቋም ዋና ስራ አስኬያጅ አቶ ጉሌድ አው-አሊ ካህን ይገኛሉ።ይህ ጉዞ ዋና አላማ  በኢ.ሶ.ክ ተወላጅ ዲያስፖራ ኮሚኒቲ በሰሜን አሜርካ  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ያደረገዉን የመጀመርያው ታሪካዊው  የስራ ጉብኝታቸዉን አስመልክቶ ለሚደረገው ታላቅ መድረክ ድጋፍ ለመስጠት መሆኑና ለመካፈል እንደሆነ አቶ ከደር አስታውቋል፡፡ ይህ በኢንዲህ እንዳለ የኢ.ሶ.ክ.መ በልማት፣ በሰላምና በመልካም አስተዳደር ያስመዘገባቸዉን ስኬቶች ቀጣይነት እንድኖረው በስብሰበው ላይ እንደምወያይም ይጠበቃል፡፡      

 

Amharic News 21_11_10
{youtube}qs4R7tSsZOc
{/youtube}


Amharic News 20_11_10
{youtube}R-foOjWmBV4{/youtube}


Amharic News 19_11_10

{youtube}HFcch8uQyMs{/youtube}


Amharic News 18_11_10
{youtube}ZC6Kl7kmx4A{/youtube}


Amharic News 17_10_10
{youtube}JyZnLiG40Bk
{/youtube}


Amharic News 16_10_10

{youtube}PtfXBQeW3U0{/youtube}


Amharic News 15_10_10

{youtube}Gk_JWeevQgQ{/youtube}


Amharic News 14_10_10
{youtube}YmZzFQZSSEQ{/youtube}


Amharic News 13_10_10
{youtube}QYRb46_8d-I
{/youtube}


Amharic News 12_10_10

{youtube}0Reuz6vjHy0{/youtube}


Amharic News 11_10_10
{youtube}9_ge_jmnagM{/youtube}