ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የመንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ ተገለጸ (2)

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሚያዝያ 9/2010..እንደምታወቀው በየአመት ረመዳን ወር ሳይገባ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት ለቀናት የሚዘልቅ የጋራ ምክክር መድረክ ይካሄዳል።በመሆኑም ከረመዳን ወር በፊት የሚካሄደው የክልሉ መንግስትና ህዝብ የጋራ መድረክ በዘንድሮ በፋፈን ዞን በአውበሬ ወረዳ እንደሚዘጋጅ መንግስት አስታውቀዋል።

በተጠማሪም ጉባኤው በአውበሬ ከተማ 3ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከግንቦት አንድ እስከ ግንቦት 3/2010ዓም የሚዘልቅ ከመሆኑ ባሻገር ከረመዳን ወር 3ቀናት ያህል እንደምቀድምም ታውቀዋል። የጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ በዚህ ሳምንት ውስጥ ወደ አስተናጋጁ ከተማ አውበሬን ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ የሚመራው ልዑኳን ቡዱን ወደ ክልሉ ርዕሰመዲና ተመለሱ (2)

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤ሚያዝያ 8/2010ዓም.በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ ኡመርና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ፤የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ ሊቀመንበር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ የሚመራው የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ልዑኳን ቡዱን ወደ ክልሉ ርዕሰመዲና ተመለሱ።ልዑኳን ቡዱኑ በትላንትና እለት በኢፌደሪ መንግስትና በሀገሪቱ ብሔር፤ብሼረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች መካከል በሀገሪቱ ርዕሰመዲና በአዲስአበባ በተካሄደው ምክክር መድረክ ከተካፈሉ በኋላ ወደ ክልሉ ርዕሰመዲና በሆነችው በጅግጅጋ ተመልሰዋል።ፕሬዝዳንቱ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ርዕሰመዲና በሆነችው በጅግጅጋ ከተማ ይገኛሉ።

በስዊድን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲያስፖራ ኮሙኒቲ ለክልሉ ልዕኳን ቡዱን የእራት ግብዣና ደማቅ አቀባበል አድርገዋል (2)

ስቶክሆልም (cakaaranews) ሰኞ፤ሚያዝያ 1ቀን ፤ 2010ዓ.ም በስዊድን ሀገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላት በተለይ የሊባን ዞን ተወላጆች  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ንግድ፤ትራንስፖርትና እንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ፤ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ ኢስማኢል የሚመራ የዲያስፖራና የክልሉ መንግስት ጥምር ልዕኳን ቡዱን በስቶክሆልም ከተማ ደማቅ አቀባበል እና የእራት ግብዣ እንደተረገላቸው ተገለጸ።

በተያያዜም በኢ.ሶ.ክ.መ.የንግድ፤ትራንስፖርትና እንዱስተሪ ቢሮ ኃላፊና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅ/ቤት ድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ከደር አብዲ የሚመራ ጥምር ልዕኳን ቡዱኑ በስዊድን ስቶክሆልም የሚኖሩ የሊባን ዞን ዲያስፖራ አባላት በክልሉ እየተከናወነ ያለው ዘርፈብዙ የሰላም፤የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ሁሌም መደገፋቸውን ለልዑኳን ቡዱኑ ገልጸዋል።በተጨማሪም ለልዕኳን ቡዱኑ በተደረገው ደማቅ አቀባበልና ልዩ የእራት ግብዣ የቡድን መሪው የላቀ ምስገናን አቅርበዋል።

የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተለያዩ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች ለተወጣጡ 25ሺህ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አነጋገሩ (2)

አዲስአበባ(cakaaranews)እሁድ፤ሚያዝያ 7/2010ዓም.የኢፌደሪ መንግስት የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ላይ እንደምትገኝ ከማንም ያልተሰወረ ትክክለኛ ጉዳይ ነው።በዚህም ከተለያዩ ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ለተወጣጡ 25ሺህ የሚሆኑ የብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተወካዮች፤የኢፌደሪ መንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት፤የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የዘጠኙ ክልሎች ርዕሳንመስተዳደሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ካንትባዎች በተገኙበት፤ህዝብና መንግስት የሚወያዩበትና የሚቀራረቡበት ምክክር መድረክ በኢስአበባ ከተማ  በሚሊንያም አደራሽ አካሄደዋል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሀገሪቱ የልማት ጀርባ አጥንት የሆኑት ወጣቶች በርካታ የልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጉና መንግስት ለወጣቶች በርካታ ስራዎች እንደሚያመቸቻችና እንደሚያሰማራም ተናግሯል።አያይዞም ወጣቶች አቅማቸውና እውቀታቸው ለልማትና ለመልካም ነገሮች እንድጠቀሙና መንግስት ሀገሪቱን ከሆላቀርነትና ደህነት የሚታወጣበት የልማት ህዳሴ ጉዞኦን የበኩላቸው ድርሻ እንደወጡ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና ሀገራዊ ጉዳዮች ለማጠናከር፤በሀገሪቷ ዴሞክራሲ ሥርዓት  ብሔራዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በማሳተፍና ሀገራዊ ጉዳዮችን ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመናጋገር፤በመወያየትና መግባባት መንግስት በቅርበት እንደሚሰራም ገልጿል።ይህ መድረክ ታሪካዊ ምክክር መድረክ ከመሆኑ ባሻገር የኢፌደሪ መንግስትና የኢትዮጵያ ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች በፍቅርና በአንድነት በጋራ ሀገራዊ አንድነት ለማጠናከርና የጋራ ሀገራችን ዴሞክራሲ፤ሰላምና መልካም አስተዳደርን በጋራ የሚንሰራበት መድረክ እንደሆነም ዶ/ር አብይ አስረድቷል።መድረኩ የህዝቦች ጥያቄዎች በአግባቡ የሚመለስና ከህዝቡ ጋር በቅርበት የሚሰራ መንግስት ለመገንባትም ይረዳል ብሏል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

በመጨረሻም የሀገራችን ብሔር፤ብሔረሰቦችና ህዝቦች የመከባበር፤የመቻቻልና በሰላም የአብሮ መኖር እሴቶቻችን ለማጠናከር መንግስት በትክረት እንደሚሰራና የመስረተልማት አውተሮችን ማሻሻል እንደምደረግም ዶር አህመድ ገልጿል።በተያያዜም ቀጣዩ ምርጫ ህዝቡ ድምጻቸው በነፃነት ለሚበጃቸው አካል መስጠት እንድምችሉና መንግስት የዴሞክራሲ ስርዓት መለኪያዎችን እንደትከተልም ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አህመድ አብራርቷል።  

 

 

 

በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን የኢሶ.ክ. መ.መዲና ደርሷል

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ቅዳሜ፣ መጋቢት 29/2010ዓ.ም. በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራ ከፍተኛ የፈዴራል መንግስት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ርዕሰ መዲና ደርሷል።በልዕኳን ቡዱኑ መካከል የኢፈዴሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኢህኣዴግ ማዕከላዊ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሺፈራው ሺጉጤ፣ የኢፈዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኢፌድሪ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ከበደ ጫኔ ፤የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳደር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ፤በኢፈዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዲብለማሲ ጉዳዮች ዳይረክተር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር እና ሌሎች የፈዴራልና የክልል መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ገራድ ውልዋል ዓለም ኣቀፍ የኣየር ማርፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ 

በተጨማሪም በኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን በጅግጅጋ የሚገኘው የገራድ ውልዋል አለም ኣቀፍ አየር ማርፊያ  ሲደርሱ የኢ.ሶ.ክ.መ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር፣ የኢፈደሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር  አቶ አህመድ ሺዴ፣ የኢፈደሪ  ሰረተኛና መህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አብዲፈታህ አብዲላሂ፣ የኢ.ሶ.ክ.መ ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ በፌዴራልና በክልል ደረጀ ያሉት ከፍተኛ ባለስልጣነት፣ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ በክልሉ ፖሊስ ማርሽ ባንድና የባህል ቡድኖች በማጀብ ደማቅ የአቀባበል ሥነ-ስርዓት ተደርጎላቸዋል፡፡

በተያያዜም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ከፍተኛው የመንግስት ልዕኳን ቡድኑ በአየር ማርፊያው እንግዳ ማረፊያ ክፍል የተወሰነ ደቂቃዎች እረፍት ከወሰዱ በኋላ ብዙሃኑ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ማህበረሰብ በመንገዶቹ ዳር ቆመው ደማቅ አቀባበል እያደረጉላቸው፣ በእግረ መንገዳቸው ለክልሉ መንግስት ካቢኔ አባላትና ለስራ ሃላፊዎች በክልሉ መንግስት በጅግጅጋ ከተማ በዱልቀበው ሰፈር የተገነባላቸዉን  ዘመናዊ መኖሪያቤቶች ጎብኝት በማድረግ ወደ ክልሉ መስተዳደር ፅ/ቤት አቅንቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ልዕኳን ቡድኑ የመስተዳደር ፅ/ቤት ከደረሱ በኋላ በቅርቡ በክልሉ መንግስት የተገዙት ዘመናዊ የእሳት አደጋ ቦቴዎችን ጎብኝቷል።በመስኪ ምልከታ ወቅትም የኢ.ሶ.ክ .መ.ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የዘመናዊ ቦቴዎቹ ጥራትና የአገልግሎት አሰጣጠቸዉን መብራርያ በመስጠት፤በመስተዳደር ፅ/ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከ95% በላይ ከአፈር የተሰረዉን ቤትም አስጎበኝቷል፡፡ አያይዞም የክልሉ ፕሬዝዳንት የአፈር ቡሉኬት ማምረቻ ማሽኑን በክልሉ ያሉት ወረዳዎችን እንደተከፋፈለላቸውን ኣክሎ ገልጿል፡፡

በተመሳሳትም ልዕኳን ቡዱኑ ወደ ሰብሰባ አዳራሽ ከመግባታቸው በፊት ለትዳር የታጩት ባልና ምስቶች የተዘጋጀላቸዉን ማረፊያ ቦታ ጎበኙ፤ ስላሙሽራዎችን ፅንስ ሀሳብና አላማ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤና የኢሶህዴፓ ሊቀመንበር ክቡር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ሲሆኑ ይህ ታሪካዊ የትዳር ትስስር ለዘመናት ግፊ ሲመሰርትባቸውና ሲጮቆኑ የነበሩት የገቦዬ ማህበረሰብ ከመላው የሶማሌ ህዝብ ዘንድ ሲገለሉና አድሎ ሲደረጉበቸው የከረሙ እንደ ነበሩ ገለፃ በመስጠት፤ በራሶ ወረዳ የተደረገው የክልሉ መንግስትና  ህዝብ የጋራ ምክክር ጉባኤ ላይ በሰፍው ተወያይቶበት፣ በክልሉ ጎሰ መሪዎችና የኀይማኖት አባቶች እንደሁም ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ታዳሚዎች በተገኙበት መድረክ ይህ የኋላቀርነት አስተሳሰብ በጭራሽ ከመሀላችን እንዲወገድ የተስማማንበት መድረክ እንደ ነበረም ኣክሎም ገልጿል፡፡  አያይዞም ይህን የኋላ ቀርነት አስተሳሰብ ለማስወገድ የተጠቀመበት መጀመሪያ ስልት ከገቦዬ ጎሳና ከሌሎች የኢትዮጵያ ሶማሌ ጎሳዎችን መካከል የእርስ በእርስ በትዳር እንድተሳሰሩ በማድረግና እንደ መፍትሄ የተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩልም ሙሺራዎቹ በበኩላቸው የተሰማቸው ደስታ በኢፈዴሪ ጣቅላይ ሚኒስትር የሚመራው ልዕኳን ቡድን በመድለጽ፤ የክልሉ መንግስትና መሪው ድርጅት ኢሶህዴፓ የሚያደርጉት ታሪካዊ የትዳር ትስስር ምንግዜም በሶማሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ወርቃማ አጋጣሚ መሆኑንም አስረድቷል።በተጨማሪም መንግስት በራሶ ወረዳ ላይ የገበዉን ቃል በተግበር አሰይቶናል፣ ይህ ደግሞ የክልላችን መንግስት ለህዝቡ ያለዉን ፍቅር እንደሆነም አስታየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

Amharic News 21_11_10
{youtube}qs4R7tSsZOc
{/youtube}


Amharic News 20_11_10
{youtube}R-foOjWmBV4{/youtube}


Amharic News 19_11_10

{youtube}HFcch8uQyMs{/youtube}


Amharic News 18_11_10
{youtube}ZC6Kl7kmx4A{/youtube}


Amharic News 17_10_10
{youtube}JyZnLiG40Bk
{/youtube}


Amharic News 16_10_10

{youtube}PtfXBQeW3U0{/youtube}


Amharic News 15_10_10

{youtube}Gk_JWeevQgQ{/youtube}


Amharic News 14_10_10
{youtube}YmZzFQZSSEQ{/youtube}


Amharic News 13_10_10
{youtube}QYRb46_8d-I
{/youtube}


Amharic News 12_10_10

{youtube}0Reuz6vjHy0{/youtube}


Amharic News 11_10_10
{youtube}9_ge_jmnagM{/youtube}