የኢ.ሶ.ክ.መ. ካቢኔ አባላት በአዲስ አበባው ቦምብ ፍንዳታ የተጎዱ ወገኖች የ15 ሚልዮን ብርለገሰ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ዕሮብ፤ሰኔ 20/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የስራ አስፈጻሚ አባላትና ካቢኔ አካላት በዛሬው እለው በክቡር ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር መሪነት ባካሄዱት የአስቹኳ ስብስባ በመዲናችን አዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ባለፈው ሰኔ 16 ቀን በዜጎቻችን ላይ በተፈጸመው የቦምብ ፍንዳታ የተጎዱ ወገኖች የ15 ሚልዮን ብር ድጋፍ ለመሰጠት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕረዝዳንት በክልሉ ርዕሰ መዲና የተገነቡ የጋራ መኖሪያቤቶች አስመረቀ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ማክሰኞ፤ሰኔ 19/2010.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕረዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ በክልሉ ርዕሰ መዲና በጅግጅጋ ከተማ በዘመናዊ መልኩ የተገነቡና እያንዳንዱ በውስጡ 9ክፈሎች ያቀፈ 130  የጋራ መኖሪያቤቶችን በዛሬ እለት አስመረቀዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ዋና ከተማ በሆነችው በጅግጅጋ የሚኖሩ ህብረተረሰብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ  የህዝቡ የመኖሪያ ቤቶች ጥያቄ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀነስ ሲሆን የነበረውን የመኖሪያቤቶች እጥረትም በእጥፍ እንደሚቀርፍም ተገልጿል። በተያያዜም ይህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቀድሞ የመከላኪያ ካምፕ በገረብአሴ ወይንም ሸውሊ በመባል የሚታወቀው አዲስ ሰፈር የተሰራ ሲሆን በከተማው ውበትም ትልቅ ሚና እንደምጫወትም የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

በጋራ መኖሪያቤቹ ግንባታ ወቅትም በርካታ የከተማውና የክልሉ ወጣቶች ኑሮ በማሻሻል የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውም እንዳሳደገም ተገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕረዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ ሞሀሙድ ኡመር በቀድሞ አየር ኃይል ሰፈር የተገነቡና እያንዳንዱ 10 ክፍሎች የሚይዝ 30 G+1 የጋራ መኖሪያ ቤቶችም አስመርቋል።በዚህም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አጭር ጊዜ ውስጥ ከሶስት ወራት በማይበልጥ በቀልጣፋና በአማረ መልክ  የሰሩት የክልሉ ቤቶች ልማት ኢንተርፕሬዝ ᎓የግል ኮንተራክተሮች᎓የክልሉ ኢንጅኔሮችና በጋራ መኖሪያቤቶቹ  ግንባታ ላይ ሌሎች ጥሩ አስተዋጸኦ ላደረጉት ባላሙያዎችና ድርጅቶችም ክቡር ፕሬዝዳንቱ የላቀ ምስገና አቅርበዋል።

ሌላ በኩል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ሳይሆን የክልሉ ሁለተኛ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አካል ሆኖ በሁሉም የክልሉ ከተማ መስተዳደሮችና ወረዳዎችም በሰፊው እየተገነባና ካሁን በፊትም ተገንብቶ ለአገልግሎት ከማብቃታቸው ባሻገር የክልሉ ህዝብ የመስረተልማት ጥያቄ በአግባቡ የሚመለስ ከMሆናቸው በዘለሌ የከተሞች እድገትና ውበትም የላቀ ድርሻ ይጫወታሉ ተብሎ ይታመናል።

በመጨረሻም በጅግጅጋ ከተማ የተገነቡና የተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የከተማው እድገት᎓ውበትና የህብረተሰቡን ጥያቄ የሚመለስ ነው ሲሉ የከተማው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት ዛሬ በአዲስ አበበ የደረሠውን የቦምብ ጥቃት እንደሚያወግዝ በከባድ አቋም ገልጿል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ16/2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢሶህዴፓ)የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአዲስ አበበ በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ የቦምብ ፍንዳታ ያቀነባበሩትን፣ የፈጸሙትን እና ከዚህ አስጸያፊ አስነዋሪና ድርጊት በስተጀርባ ያሉትን ግለሰቦች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አንድነት የማይወዱና የሀገራችንን ህዝቦች ለመበታተን፣ ለማፋጀት እንዲሁም ሊያባሉን የፈለጉ የአሸባሪዎች ድርጊት ነው ሲሉ መላው የክልሉ ህዝብና መንግሥት በከባድ አቋማቸው ማውገዛቸውን ገልፀዋል።

በመቀጠልም የኢሶህዴፓ፣ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት እና መላው የክልሉ ህዝብ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ በደረሰው የቦምብ ፍንዳታ ለተጎዱ ወገኖቻችን እና ቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ጥልቅ መራራ ሃዘን እየገለፀ አስጸያፊ ድርግቱን በከባድ አቋም እንደሚያወግዝ ይገልፃል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሃዘን መግለጫ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ቅዳሜ፤ሰኔ 16/2010ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ከተመረጠ ወዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሃገሪቱ በርካታ ስኬቶች፣ የብሔራዊ መግባባት እርምጃዎች እና ተግባራት እንደተፈጠሩ እርግጥ ነው።

ስለሆነም በራሴ በክልሉ መንግሥትና በክልሉ ህዝብ ሥም ልገልፅ የምፈልገው በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት በተገኙት አመርቂ እና ተጨባጭ የልማት ስኬቶች እንዲሁም ድሎች መመዝገብ በበኩሌ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በዛሬው እለት ሰኔ 16/2010 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ ጁን 23/2018 በመዲናችን አዲስ አበባ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የሃገሪቷ ህዝቦች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ደጋፊነት በሠላማዊ ሰልፍ ባሳዩበት አስደናቂ መድረክ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተገኝተው ንግግራቸውን ባጠናቀቁበት ወቅት አሸባሪዎች በዜጎቻችን ላይ የሽብር ጥቃት ፈጽመዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት በራሱ በክልሉ መንግሥት እና በክልሉ ህዝብ ሥም ሲናገሩ ፍርሃት በተሞላበት መልኩ የአሻባሪ ቦምብ ጥቃት የፈጸሙትን አስፀያፊዎች ድርጊት እያውገዙ በጥቃቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የሃገራችን ህዝቦች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ ፤ በጥቃቱ ለተጎዱት ዜጎቻችን በሚደረግ ድጋፍ ሁሉ የክልሉ መንግሥት በቀዳሚነት የበኩሉን እንደሚወጣ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።

 

በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ድጋፍ በኢትዮጵያ ሶማሌ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባላሙያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ስልጠና አዘጋጀ

ጅግጀጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሰኔ 12/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ድጋፍ የሚደረግለትና በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሞያን ለመደገፍ ታስቦ በተዘጋጀ ውድድር ላይ ተሳታፊዎችን ለማብቃት የተዘጋጀ ስልጠና በዘሬው እለት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ መካሄዱ ተገለፀ። በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የክልሉ ሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሞያዎችም ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረገው እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የጋዜጠኞችን ሞያ ለመደገፍ ብሎም የክህሎት ውድድርን ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የምርመራ ጋዜጠኝነትን በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ለማደረግ የሚያስችል ክህሎት በማሳደግ የጋዜጠኞችን ሞያና አቅም የማበልፀግ አላማ እንዳለውም የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። በዚህ ስልጠና ላይ ጋዜጠኞች የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት USAID እና የአሜሪካን መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከያ ማዕከል CDC በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስለሚካሄዱት የሥራ እንቅስቃሴ ግንዛቤ በማስጨበጥ በእነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የጋዜጠኝነት ሞያን ተከትለው የምርመራ ዘገባ እንዲሰሩ ታስቦም የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ ላይም የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፈርሃን መሀሙድ፤የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅኔር ኢድሪስ እስማኢል እንድሁም የክልሉ ሚዲያና የኮሙኒኬሽን አመራርና ባላሙያዎችም ተካፈለዋል።በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት   በክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅኔር ኢድሪስ እስማኢል አብዲ  "በቅድሚያም ሁላችሁም እዚህ የተገኛችሁትን እያመሰገንኩ ይህ ስልጠና በመዘጋጀቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል ስልጠናው በልማት ጋዜጠኝነት ላይ የልምድ ማጎለበቻ መሆኑን እየገለፅኩ በአቅም ግንባታ ስልጠናው የሚሳተፉ ጋዜጠኞች ከስልጠናው በልማት እና በምርመራ ጋዜጠኝነት ብዙ ልምድ ይቀስማሉ ይህም ለሚዲያ ባለሞያዎች ትልቅ ጠቃሜታን ያበረክታል። ከዚህምበተጨማሪ  በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን የፕሬስ ነፃነት በመጠቀም የክልሉ ሚዲያ ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ብሎም የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎችን ለህዝብ በማድረስ በህዝብ እና መንግሥት መካከል አገናኝ ድልድይ በመሆን የተጣለባቸው ሃላፊነት ይበልጥ እንዲወጡ የሚያስችላቸውም ነው። እንደሚታወቀው የክልላችን መንግሥት የማህበረሠቡን የሚዲያ አማራጮችን በማስፋፋት ከሚኒ ሚዲያ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች ተደራሽነትን እያስፋፋ ይገኛል። እነዚህ ተቋማትም ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ ሕዝቡ በማድረሱ ረገድ ስኬታማ ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ። በመጨረሻም ስልጠናውን ያዘጋጁትን የአሜሪካን ኤምባሲ አካላትን እያመሰገንኩ የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስባለሁ"  ሲሉ ተናግሯል።

በመጨረሻም ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት በመጀመሪያው ክፍል ከየክልሉ ለተውጣጡና በሥራ ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል ይህም በጤና፣ ትምህርትና ግብርና ብሎም ሠብዓዊ እርዳታን በመሳሰሉት የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የምርመራ ዘገባን መስራት የሚያስችሉ ክህሎቶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ይሆናል።  በሁለተኛው ክፍል ተሳታፊ ጋዜጠኞች በክልላቸው ልማት ተኮር ዘገባን በመሥራት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ላይ እንዲሳተፉና ተጨባጭ የሆኑ ዘገባዎች እንዲያቀርቡ የሚያግዝ መሆኑን የስልጠናው አዘጋጆች ገልፀዋል።

Amharic News 21_11_10
{youtube}qs4R7tSsZOc
{/youtube}


Amharic News 20_11_10
{youtube}R-foOjWmBV4{/youtube}


Amharic News 19_11_10

{youtube}HFcch8uQyMs{/youtube}


Amharic News 18_11_10
{youtube}ZC6Kl7kmx4A{/youtube}


Amharic News 17_10_10
{youtube}JyZnLiG40Bk
{/youtube}


Amharic News 16_10_10

{youtube}PtfXBQeW3U0{/youtube}


Amharic News 15_10_10

{youtube}Gk_JWeevQgQ{/youtube}


Amharic News 14_10_10
{youtube}YmZzFQZSSEQ{/youtube}


Amharic News 13_10_10
{youtube}QYRb46_8d-I
{/youtube}


Amharic News 12_10_10

{youtube}0Reuz6vjHy0{/youtube}


Amharic News 11_10_10
{youtube}9_ge_jmnagM{/youtube}