በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት የሚመራ የክልሉ ከፈተኛ አመራር ልዑካን ቡዱን ወደ ቀይ አፈር የተቆፈሩት የውሃ ፖሮጀክቶች አመሩ፡፡

Jigjiga(Cakaaranews) ሀሙስ መስከረም 11, 2010 ዓም.  በዛሬ እለት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ አብድ መሀሙድ ኡመር የሚመራ የክልሉ ከፈተኛ አመራር ልዑካን ቡዱን ከጅግጅጋ በመነሳት 160..የክልሉ ከፍተኛ የመሬት አቀማመጥ ባላቸው የቀይ አፈርና አሸዋማ አከባቢዎች ላይ 2 ዙር የተቆፈሩት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ፖሮጀክት ለማስመረቅ አቀኑ፡፡ይህ የክልሉ አመራር ልዑካን ቡዱን በቢርቆት፡ጉናገዶ፡መርሲን፡ዳኖት በንሀቡባና ጋሻሞ ወረዳዎች የተሠሩ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክት ያስመሪቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡ በመጨረሻም ለዘመናት የቆየውን የውሃ ችግርን ዘላቂ መፍትሔ ሲሆን 154 አባ-እማ ወራዎችና በርካታ የአከባቢው እንስሳትም ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡