የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ከተለያዩ ህብረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ተወያዩ፡፡

Jigjiga(Cakaaranews) ሀሙስ  መስከረም18 2010 ዓም.  በኢትዮጵያ ሶማሌና ኦሮሚያ አዋሳኝ አከባቢዎች የሚፈጠሩ ግጭቶችን ከመነሻው ለመፍታት የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግር ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሰት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር እና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ መሀመድረሽድ ኢሣቅ ከአገር ሸማግሌዎች፣ ከንግድ ማህበረሰብ አባላት የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት መድረግ በጅግጅጋ ከተማ አካሄደዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አብዲ መሐሙድ በሰጡት መብራሪያ የኢትዮጵያ ሶማሊና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አከባዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች መንግስት ከሚያደርግላቸው የምግብ፣የመጠሊያና የህክምና ድጋፍ ጉን ለጉን የህብረተሰቡን ተሳትፎ አስፈላጊ ነው፡፡

ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ለማሰባሰብ መላው የክልሉ ነዋሪዎች እና የዲያስፖራ አባላት ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጠይቋል፡፡ተፈናቃዮችን መልሶ እንዲቋቋሙ ልዩ ድጋፍ በማድረግ ከጎናቸው መቆም ከሁሉም ህብረተሰብ ክፍል እንደሚጠበቅ ነው የተናገሩት፡፡

ተፈናቃዮችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም ክልላዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ በመድረኩ የተመረጠ ሲሆን ለድጋፍ አገልግሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በሀዋላ አካውንት መከፈቱንም ተገልጸዋል፡፡

ክቡር ፕሬዝዳንቱ እንዳብራሩት አዋሳኝ የኢትዮጵያ ሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎች ነዋሪዎች ለአመታት የነበረባቸው መሰረታዊ ልማት እጥረት ምክንያት ሲፈጠር የቆዩ ግጭቶችን ለማስወገድ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ በርካታ የገጠር መንገዶችና ድልድሎች በእነዚሁ አከባቢዎች መገንባታቸውን ነው የተናገሩት ፡፡

የክልሉ ፕሬዚዳንት ባለፈው ሳምንት በጀረር፣ቆራሓይና ዶሎ ዞኖች ያካሄዱትን ግዙፍ የውሃ ፕሮጅክቶች ምረቃ የህዝቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡን እጅጉን የአርብቶ አደሩን የውሃ ችግር ያስወገዱ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በዚህም የክልሉ መንግስት የውሃ እጥረትን ለመቅረፍ ባለፈው ሳምንት ሦስት ዞኖች የሚያስተሳስርና ከመነሻው ቢርቆድ፣ ጉነገዶ፣ ዲግ፣ መርስንና ጋሻሞ ወረዳዎች በማገናኘት 250 ኪሎ ሜትር ጥልቅ ጉድጓዶችና የውሃ ቧንቧ የተዘረጋ ሲሆን በየ5ኪሎ ሜትሩ የእንስሳት ውሃ መጠቀሚያ ገንዳና ማህበረሰቡ ውሃ የሚያገኝበት 36 ቦኖዎች ተገንብቷል፡፡

በጀረር ዞን ጋሻሙ ወረዳ በተፈጥሮ መሬት አቀማመጥ ምክንያት በቅርብ ርቀት ውሃ የማይገኝባቸው አከባቢዎች መካከል ባን-ሀጉጋ፣ ኤልበሓይና በሊ-ጀኖ ጋሻሞ ከተማ 150 ኪ.ሜ.ርዝመት ለሚገነቡ የውሃ ፕሮጀክቶች በርእሰ መስተዳደሩ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጠዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ለተፈናቃዮች መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ድጋፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብቷ፡፡

የተፈናቃዮች ችግር የወገኖቻቸው ችግር በመሆኑ የራሳቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚያደርጉት ቃል ገቡ፡፡ የክልሉ መንግስት ዘርፋ ብዙ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ስኬታማ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል፡፡