የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ህብረተሰብ የምግብ፡መድኃኒትና የቤት ቁሳቁሶች እርዳታ ለገሴ፡፡

ቆለቺ(cakaaranews) ሀሙስ,መስከረም 25/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት በቆለቺ ቀበሌ የሚገኙና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ  የኢትዮጵያ ሶማሌ ህብረተሰብ የምግብ፡የመድኃኒትና የቤት ቁሳቁስ እርዳታ ለገሴ፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል መንግስት መስተዳደር ፅ/ቤት ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዴቅ አብዱላሂ፡የክልሉ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን መሀመድና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃለፊ አቶ ኢብራህም ኣደን መሀድ የክልሉ መንግስት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆችና በቆለቺ ቀበሌ የመልሶ ማቋቋም የተደረገለት ማህበረሰብ የምግብ፡መድኃኒትና የቤት ቁሳቁሶች እርዳታ አደረሱ፡፡

የክልሉ ሚዲያ ለተቀናቃዮችሁ መንግስት እያደረገለት ያለው ድጋፍና በኑሯቸው ላይ የታየ ለውጥ በተጠየቀበት ግዜ፡ተፈናቃዮችሁ የክልሉ መንግስት በተከታታይ እያደረሰ ያለው ድጋፍ የላቀ ምስገና ከማቅረባቸው ባሻገር የክልሉ መንግስት ለሰው ልጅ መስረታዊ ነገሮች እንደመኖሪያ ቤቶች፡ምግብና መድሃኒት ሁሉ አሞልቶልናል ሲሉ ተናግሯል፡፡ከዚህ በተያያዜም በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የቤተሰባቸው አባላት በፊት ለፊታችን እያዩ መታረዱና፡በተፈናቃዮች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ማድረሳቸውና ንብረታቸው መዘረፉም አሳወቋል፡፡

 በሌላ በኩል ተፈናቃዮችሁ በኦሮሞ ክልል ለረጅም አመታት የኖሩ ከመሆናቸው ባላፈ በአገራችን ኢትየጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርግቶች ይደርሰናል ብለን አላሰብንም ብሏል፡፡በመጨረሻም የክልሉ መንግስት በኑሯቸው በጣም እንዳሻሻለ ከመናገራቸው ባሻገር የክልሉ መንግስት ለተፈናቃዮችሁ በተከታታይ እያደረገ ያለው ርብርብና ድጋፍም የላቀ ምስገና አቀርቧል፡፡