በቆለቺ ቀበሌ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች በዘላቂነት እንድቋቋሙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፎቸው የሚያጠናከሩበት የምክክር መድረክ ተካሄዷል

ጅግጅጋ (cakaaranews)ኡሁድ መስከረም 28/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ አስተባባሪነት በቆለቺ ቀበሌ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ የተደረገለትና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ወገኖች በዘላቂነት እንድቋቋሙ ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳትፎቸው የሚያጠናከሩበት ምክክር መድረክ በክልሉ ርዕስ-መዲና በጅግጅጋ ከተማ ተካሄዷል፡፡በመድረኩ ላይም ከአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ጋር ባላድርሻ የሆኑት መንግስታዊና መንግስታዊ  ያልሆኑ ተቋማትም ተገኘቷል፡፡

በመድረኩ መዝግያ ሥነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ/ሶ/ክ/መ.የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አንዋር አሊ  ምክክር መድረኩ ለቀናት ያህል የቀጠለ ቢሆንም የመድረኩ አላማ የክልሉ መንግስት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶመሌ ተወላጅ ማህበረሰብን በቆለቺ ቀበሌ የመልሶ ማቋቋም መጠሊያ ጣቢያ መስራቱ የሚታወስ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃዮች  በዘላቂነት እንድቋቋሙና በክልሉ የሚገኙ ለጋሽ ድርጅቶችና ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የበኩላቸው ተሳትፎ የሚያጠናከሩበት የጋራ  መፈክር  ከሆኑ ባሻገር ተፈናቃይ ማህበረሰብን በዋናዋና የመስረተ-ልማት ጉዳዮች እንደ-ንፁህ የመጠጥ ውሃ፡ጤና፡የምግብ ዋስትናና መሰል ጉዳዮችን በዘላቂነት እንድቋቋሙ የክልሉ መንግሰት ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር የጋራ  ስተራቴጂዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀመጡበት መድረክ እንደነበረ አስረድቷል፡፡በመድረኩ ላይም ከአለማቀፍ ድርጅቶችና የክልሉ ሰክተር መ/ቤቶች የተወጣጡ አካላት መሳተፋቸውም ጠቁሟል፡፡    

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና በአገር ውስጥና በባህር ማዶ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ተፈናቃይ ወገኖችን ለመረዳትና በዘላቂነት ለማቋቋም ከፍተኛ እንቀስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡