የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሲቪል ሴርቪስና ሰው ኃይል ልማት ቢሮ የሥራ ሚዛና እቅዱ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገለፀዋል።

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ፤ ጥቅምት 27/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ሲቪል ሴርቪስና የሰው ኃይል ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኮሬ በክልሉ ሰክተር መ/ቤቶች ላይ ሲተገብር የቆየውን የሥራ ሚዛና( JEG) መርሃግብር ከ90% ባላይ እንዳጠናቀቀና በዘንድሮ በ2010ዓ.ም. በሁሉም የክልሉ ወረዳዎችና በከተማ አስተዳደሮቹ የሚገኙ የመንግስት መስሪያቤቶች ተግባራዊ እንደሚያደርጉም ጠቆሟል ።

የሥራ ሚዘና ፖሮግራሙ ለሥራና ለሰረተኞችም ወሰኝ ከመሆኑ ባሻገር ለአገልገሎች አሰጣጥ ጥራትና ለክልሉ ህዝብ እርካታም ትልቅ ሚና ይጫወታል ብሏል ቢሮ ኃላፊው።በተያያዜም በሥራ ሚዛና  መርሃ ግብሩ ላይ የሰተኛው አመለካከት፤የስራ ልምድ፤የሥራ አይነትና ለስራው የሚየስፈልገው ሙያ አይነቶችን የሚትኮር ፖሮግራም ነው ብሏል ኦቶ አህመድ ኮሬ።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሲቪል ሴርቪስና ሰው ኃይል ልማት ቢሮ ከቅርብዓመታትውስጥየክልሉ መንግስት መ/ቤቶች ለህዝብ ስለሚሰጡ አገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ፤ የሰራተኞችንየአቅምግንባታና ሁሉም  የመንግስት ሥራዎችየተሻሻለ  ቴክኖሎጂ(ICT)  የተደገፉ ናቸው ብሏል