በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡዱን ወደ ራሶ አመሩ

ቀብሪደሀር(Cakaaranews) ሰኞ፤ጥር 7ቀን/2010ዓ.ም.በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡዱን ከክልሉ ዋና ከተማ በመነሳትና ከጅግጅጋ እስከ ጎዴይ በሚዘልቀው የአስፋልት መንገድ ይዞ ተጓዟል።ልዑካን በዱኑ በመሀል የሚገኙ የመስኖ ልማት ሜጋ ፖሮጀክቶች እንደ በካ፤ጎማር፤ወቸዋቺና መረኣቶ ሀፈር ዳሞችን ይጎበኛሉ።የፕሬዝዳንቱ ልዑካን ቡዱን ከፈዴራል ልዑካን ቡዱን ጋር በመሆን በነጌ እለት ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ያስመሪቃሉ። በተጨማሪም በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት የሚመራ ልዑካን ቡዱኑ ለሚቀጥለው ቀናት በአፍዴር ዞን ራሶ ወረዳ በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓና በክልሉ ህዝብ መካከል ለሚካሄደው የጋራ ኮንፈረንስ ለመካፈል ከቀብሪደሀር ወደ ራሶ ከተማ ያመራሉ ተብሎ ይጠብቃል።