በኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ ሞሀሙድ የሚመራ የፈዴራልና የክልሉ ልዑካን ቡዱን የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ በጋራ አስመርቋል

ቀብሪደሀር(cakaaranews)ሀሙስ፤ጥር 10ቀን/2010ዓ.ም.በኢ.ሶ.ክ.መ.በቆራሔይ ዞን፤በቀብሪደሀር ከተማ በኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ አብዲ ሞሀሙድ ኡመር የሚመራ የፈዴራልና የክልል ልዑካን ቡዱን በአማሬ መልኩ የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ  በጋራ  አስመርቋል።በምርቃት ስነ-ሥርዓቱ ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሞሀሙድ፤የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ትምህርት ሚንስተሪ ሚንስተር ዶር ጥላየ ጌጤ፤የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ትምህርት ሚንስቴሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚንስተር ዴታ ዶር  ሳሙኤል ኪፍሌ፤የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር ዩሱፍ መሀመድ አሊ፤የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች፤የአከባቢው አገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶች፤እንድሁም ሌሎች የፈዴራልና የክልል ክቡር እንግዶችም ተገኝቷል።

በ2008ዓ.ም በሚንስተሮች ም/ቤት በሀገሪቷ እንድገነቡ ከጸደቁት 11 አዳዲስ ዩኒቬርሲቲዎች መካከል አንዷ ቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ ናት፤የዩኒቬርሲቲው ግንባታ ከ2 አመታት ባነሴ ጊዜ በ11 አገር አቋራጭ ድርጅቶች የተገነባ ሲሆን ዩኒቬርሲቲው በትላንትና እለት በኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ አብዲ መሀሙድና በኢ.ፈ.ዴ.ሪ.የትምህርት ሚንስተሪ ሚንስተር ዶር ጥላየ ጌጤ በጋራ  ተመርቋል።

በዩኒቬርሲቲው ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ  ኡመር በመድረኩ ላይ ታካፋይ የነበሩት የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ትምህርት ሚንስተር ዶር ጥላየ ጌጤና በትምህርት ሚንስቴሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚንስተር ዴታ ዶር  ሳሙኤል ኪፍሌ፤የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር ዩሱፍ መሀመድና የዩኒቬርሲቲው ቦርድ አመራር፤የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት እንድሁም ለአከባቢው አገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶችን ለዩኒቬርሲቲው ግንባታ በወቅቱ ለማጠናቀቅ ላደረጉት ጥብቅ  ክትትልና ቆራጥነትን በማመስገን ፤ከደርግ አገዛዝ ውድቀት በኃላ በሀገሩቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚክ እድገት ከማስመዝገቡ ባሻገር የሀገራችን ኢኖሚክ ላውጡ ፍትሃዊና ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ ነው ብሏል።በተጨማሪም የሀገራችን ቀድሞ መንግስታት ለኢትዮጵያ ሶማሌ አርብቶአደሩ ማህበረሰብ አይደለም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መገንባትና የቀለም ትምህርት ማዕከላት ሳይገነቡላትና ህብረተሰቡ በፊደልና ቁጥር መጻፍ ሳያስችሉ፤እንድሁም ለክልሉ ህዝብ ትምህርት ተደራሽና ተጠቃሚ ሳያደርጉ ያለፉት ሥርዓቶች እንደነበሩም ፕሬዝዳንቱ ጠቆሟል።

በሌላ በኩል ባለፉት 26 አመታት በተላይ በመጨረሻው አስርተ-አመታት የክልሉ ህዝብና መንግስት ከፈዴራል መንግስት ጋር በመሆን የክልሉ ህዝብ ኑሮ ለማሻሽልና የአርቢቶአደሩ ማህበረሰብ አኗኗር ወደ ከፊልአርቢቶአደርነት የሚያሸጋገሩ በርካታ ሜጋ ፖሮጀክቶች ከመፈጸማቸው ባሻገር በዛሬ እለት በታሪካዊዯ የምስራቅ መዲና በቀብሪደሐር ከተማ በሚናስመርቀው ቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ የልማቱ ትልቅ ማሳያናት ብሏል ክቡር ፕሬዝዳንቱ።በክልሉ አከባቢ ለሚገኙ የኪርሰ ምድርና ከምድር ባላይ ያለው ውሃ ለማውጣትና በክልሉ ሆነ በሀገሩቷ ለሚገኙ ያልተነካ ተፈጥሮ ሀብቶቻችን ትክክለኛ ጥናትና ምርምሮች ለማካሄድ ዩኒቬርሲቲው ትልቅ አስታዋጸኦ እንደሚኖረውም ፕሬዝዳንቱ አብራርቷል።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ የመጀመሪያ አመት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ላሉ አዲሰ ተማሪዎች፤በተለያዩ የዩኒቬርሲቲው የሥራ እርኪኖች ለሚገኙ ሰረተኞች፤የዩኒቬርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራር አባላት፤የአከባቢው አገር ሽማግሌዎችና የእምነት አባቶችና እንድሁም ሌሎች የፈዴራልና የክልል ባላድርሻ አካላቱ በዩኒቬርሲቲው ትምህርት ጥራት በባላቤትነት በጋር እንድሰሩ አሳስቧል

በሌላ በኩል የኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ትምህርት ሚንስተር ዶር ጥላየ ጌጤ በበኩላቸው በርካታ የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ አቻ ዩኒቬርሲቲዎች ግንባታ ባታቀደው ጊዜ እንዳልተጠናቀቀ ከመግለጻቸው ባሻገር የቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ ግንባታ ከዘገዩ ዩንቨርስቲዎች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራር በወሰዱት ቆራጥ የአመራር ውሳኔ ለዩኒቬርሲቲው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች ክልሉ ከራሱ በጀት በሟሟላት ዩኒቬርሲቲው ለመጀመሪያ ዙር 1500 አዲስ ተማሪዎች እንድመቀበልና ሁሉም የመማር ማስተማር አገልግሎትን እንድሰጥና በዛሬ እለት ለምርቃት እንድበቃ ምክያት ሆኗል ብሏል።

በመሳሳይም የቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶር ዩሱፍ መሀመድ እስካሁን ለዩኒቬርሲቲው የመጀመሪ ምዕራፍ ግንባታ 740 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሲሆን ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተወጣጡ 1500 የመጀመሪያ አመት አዲስ ተማሪዎች በመቀበልና ተቋሙ ሁሉም የመማር ማስተማር አገልግሎትን ከመጀመሩ ባለፈ ለተማሪዎቹ በእንግዳ ተቀባይነት የሚታወቁ የአከባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል አደርጎላቿል።

በሌላ በኩል የቀብሪደሀር ከተማ አስተዳደር ሀገር ሽማግሎችና እምነት አባቶች ዩኒቬርሲቲው ለአከባቢው ማህበረሰብ፤ለክልሉና ብሎም ለአገሪቱ ህዝብ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድቷል።በመጨረሻም በ11ዱ አዳዲስ ዩኒቬረሲቲዎች እንካሁን ከተመረቁት መካከል ቀብሪደሀር ዩኒቬርሲቲ 3ተኛ ከመሆኗ ባለፈ በዩኒቨርሲቲ ግንባታ ከልባቸው አስተዋጸኦ ላደረጉት የክልልና ፈዴራል ተቋማትና ግለሰቦችም በክልሉ መንግስትና በኢ.ፈ.ዴ.ሪ.ትምህርት ሚንስቴር ሽልማት ተበርኪቶላቿል።