11ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የጋራ ህዝባዊ ኮንፌረንስ በራሶ ከተማ ተጀመረ

ራሶ(Cakaaranews) አሁጥ ጥር 13/2010ዓ.ም. 11ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት የጋራ ህዝባዊ  ኮንፌረንስ በአፍዴር ዞን በራሶ ወረዳ መቀመጪያ የሆነችው ራሶ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።በመድረኩ ላይ የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ  አብዲ ሞሀሙድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት፤በኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. የድሬ ደዋ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር አባላት፤እንድሁም ከ11ዱ የኢ.ሶ.ክ.መ. ዞኖች፤ከክልሉ 93 ወረዳዎችና 6ቱ ከተማ መስተዳደሮች የተወጣጡ ከ3000 ባላይ የሚሆኑ ታዳሚዎች ተገኝቷል።

በኮንፌረንሱ ላይ የመክፈቻ  ንግግር ያቀረቡት የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንትክቡርአቶ አብዲ ሞሀሙድ ኡመር ጉባኤ ዋና አላማ ባለፍው 10 አመታት በክልሉ መንግስትና ህዝብ የተከናወኑ የልማት፤የሰላም፤የመልካም አስተዳደር፤ እንድሁም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በባህርማዶና ሀገር ውስጥ የተረሰሩ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት  ሥራዎቻችን ውጤት የሚገመገምበትና ከ10አመታት በፊት ክልሉ የነበረበት ሁኔታዎች አሁን ክልሉ የደረሰበት ዘርፈብዙ የልማት ስራዎች  የሚነጻፀርበትና እንድሁም የቀጣይ ትክረት አቅጣጫዎች የሚመክርበት ታላቅ የህዝብ ኮንፌረንስ ነው ብሏል።በተጨማሪም በመድረኩ ላይ በሶማሌ ቤሔረሰብ ውስጥ የሚገኙ ጎሳዎች መካከል በተላይም በአናሳ የገቦየ ማህበረስብ ላይ የሚደረገው ትርጉም አልባ ንቀት፤ ጭቆናናሁሉም  በገቦያ ማህበረሰብ ላይ የሚደረጉ ጎጂ ልማዳዊ  ድርጊቶች በዚህ ጉባኤ ላይ ይወገዳል ክቡር ፕሬዝዳንቱ ተናግሯል ።

 

በመጨረሻም 11ኛው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የጋራ ህዝባዊ ኮንፌረንሱ በአፍዴር ዞን በራሶ ከተማ እንሚቀጥል መንግስት አረጋግጧል።