የኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች የእህልና የቤት ቁሳቁስ እርዳታ አበረከቱ

ራሶ(Cakaaranews) አሁድ ጥር 13/2010ዓ.ም.  በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር የሚመራ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ  ልዑኳን  ቡዱን በአፍዴርዞን፤ራሶወረዳየመልሶማቋቋምመጠሊያጣቢያለሚገኙከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ወገኖች  በርካታ አልሚ የምግብ አይነቶችና የተለያዩ የቤት ማገልገያ ቁሳቁስና የአልባሳት ድጋፍ አበርኪቶላቿል።በተያያዜም በሺዎች የሚቆጠሩ ከኦሮሚያ ክልል  የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጅ ወገኖች የተሰጣቸው የእህል ድጋፍ የተለያዩ አልሚ የምግብ አይነቶች እንደ ሩዝ፤ሱኳር፤ወተት፤ቡስኩትና የመሳሰሉት ይገኙበታሉ።በተጨማሪም ለተፈናቃይ ወገኖች የተለያዩ ቤት ማገልገያ ቁሳቁስና በርካታ የአልባሳት አይነቶች እንደ ብርድ ልብስና አጎበርና ወዘተ በኢ.ሶ.ክ.መ.ፕሬዝዳንት የሚመራ ልዑኳን  ቡዱን ተበርኪቶላቿል።

በሌላ በኩል በራሶ መጠሊያጣቢያ ለሚገኙ ከኦሮሚያ ክልል  የተፈናቀሉ የኢትዮ- ሶማሌ ተወላጅ ወገኖች የተለያዩ የምግብ አይነቶችና ቁሳቁስ እርዳታ ላደረሱ የክልሉ መንግስት አመራር የላቀ ምስገና አቀርቧል።

 በመጨረሻም በተለያዩ የክልሉ አከባቢዎች  ለሚገኙና ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮ- ሶማሌ ቤሔር ተወላጆች የሚደረግላቸውን ድጋፍና እርዳታ ለመጀመሪያ ወይም ለመጨረሻ  ጊዜ ሳይሆን የማይቋረጥ ርብርብ ነው ብሏል አመራሩ።