በሻይጎሽ ወረዳ ሲካሄድ የነበረውን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ ተጠናቀቀ

ሻይጎሽ(Cakaaranews) ሰኞ፤ጥር 14፤2010ዓ.ም.ባለፎ ሳምንት በኢ.ሶ.ክ.መ.ቆራሔይ ዞን፤በሻይጎሽ ወረዳ በመቶዎች የቆጠሩ አይነብርሃናቸው ላጡ ዞጎች ተጠቃሚ ያደረገውን ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ ተጠናቅቋል።

ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራም በአጠቃላይ በኢ.ሶ.ክ.መ.አከባቢዎች የሚኖሩና የአይነብርሃን ችግር ያለባቸው ሶዎች ተጠቃሚ ያደረገና የበርካታ ዜጎች አይነ ብርሃን ያስመለሰ ፖሮግራም ሲሆን ባለፎ ሳምንት በሻይጎሽ ወረዳ ትክረት አደርጎ በመቶዎች የሚቆጠሩና አይነብርሃናቸው ለጡ ዞጎች በነጻ ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙን ተጠቃሚ ማድረጉን የወረዳው ጤና ቢሮ አስታውቋል።በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪኪምና ቡዱኑ ባለፎ ሳምንት በዞን ሻይጎሽ ወረዳ ሲያካሄዱ የነበረውን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገናና ህኪምና አገልግሎት  ማጠናቀቃቸውን ገልጿል።

በተያያዜም በሻይጎሽ ወረዳ አከባቢዎች የሚኖሩና አይነብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች ፖሮግራሙ  በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢ.ሶ.ክ.መ. ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠቱን አመስግኗል።በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ቡዱኑ ከሻይጎሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት ለመስጠት ወደ ጎዴ ያልፋሉ ተብሏል። ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሚሰራ ልዩና ብቸኛ ፖሮግራም ሲሆን የክልሉ ህዝብ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደረገ የጤና አገልግሎት  ፖሮግራም ነው።