ከኢትዮጵያ ሶማሌና ከኦሮሚያ ክልሎች ተፈናቃይ ወገኖች የዘላቂ መልሶ ማቋቋም የሚወያይበት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስአበባ(Cakaaranews)ሰኞ፤ጥር 21/2010.. ከኦሮሚያና ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎች በዘላቂነት ለማቋቋም የሚወያይበት መድረክ በዛሬ እለት በአዲስ አበባ ተካሄዷል።መድረኩ በኢ.... /ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ደመቀ መኮንን፤በፈዴራልና አርቢቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚንስተር አቶ ከበደ ጫኔ፤እንድሁም በቤሔራዊ አደጋ ስጋትና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሺኔር አቶ ምትኩ ካሳ የተመራ ሲሆን በውይይት መድረኩ ላይ የኢ....ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር፤የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳና ሌሎች የክልል ከፍተኛ አመራር አባላት ተካፍሏል።በምክክሩ ላይ ከሁለቱ ክልሎች የተፈናቃሉ ወገኖች በዘላቂነትና በቋሚነት ለማቋቋም በሰፊው ተወያይቶበታል።

 በመጨረሻም በሁለቱ ክልሎች መካከል የነበረውን ግጭቶች በዘላቂነት መፍትሄ እንድያገኝ ከስምምነት ተደርሶበታል።