ተንቀሳቃሽ የአይን ሂኪምና አገልግሎት በራሶ ተጀመረ

ራሶ(Cakaaranews) ሰኞ፤ጥር 28/2010ዓ.ም.የኢ.ሶ.ክ.ተንቀሳቃሽ የአይን ሂኪምና ቡዱን በአፍዴር ዞን፤በራሶ ወረዳና በራሶ ከተማ ለሚገኙ በርካታ የአይን ሞራና ሌሎች የተለያዩ የአይን በሽታዎች  ያለባቸው ነዋሪዎች ነጻ የአይን ሂኪምና አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። 

ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራም በአጠቃላይ በኢ.ሶ.ክ.መ.አከባቢዎች ለሚኖሩና የአይነብርሃን ችግር ያለባቸው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረገና የበርካታ ዜጎች አይነ ብርሃን ያስመለሰላቸው ፖሮግራም ሲሆን በዚህ ሳምንት በራሶ ወረዳ ትክረት አደርጎ አይነብርሃናቸው ለጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዞጎች በነጻ ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎትን ተጠቃሚ ማድረጉን የወረዳው አመራር አስታውቋል።በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪኪምና አገልግሎት መስጠቱን በወረዳው የሚኖሩና ብርሃናቸው አይን ሞራ  ያጋረዳቸው ከበሽታው ለመፈወስ ከፍተኛ አስታወጸኦ እንዳለው አስተዳደሩ ገልጿል።

በተያያዜም በራሶ ወረዳ አከባቢ የሚኖሩና አይነብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች  አገልግሎቱ  በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢ.ሶ.ክ.ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠቱን አመስግኗል።

በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ቡዱኑ ለአንድ ሳምንት ያህል ለራሶ ህብረተሰብ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል። ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና መርሃግብሩ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሚሰራ ልዩና ብቸኛ ፖሮግራም ሲሆን የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ያደረገ የጤና አገልግሎት ፖሮግራም መሆኑን ይታወቃል።