ለክልሉ ዘኖችና ወረዳዎች 46 ተራክተሮች መስጠታቸው ተገለጸ

ጅግጅጋ(Cakaaranews) ሰኞ ፤የካቲት 6/2010.የክልሉ ሁለተኛ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዋና ስተራቴጂ የሆነውን የመስረተልማት እቅድን ተግባራዊ  ለማድረግ ለክልሉ ዘኖችና ወረዳዎች 46 ተራክተሮች ተሰጥቷል።

በተጨማሪም የክልሉ መስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዲመሀድ መሀመድ አባሴ ለዞችና ወረዳዎች አስተዳደሮች 46 የዘመናዊ ግብርና ተራክተሮች በአስረከቡበት ወቅት አመራሩ የክልሉ  እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዋና ስተራቴጂ የሆነውን የመስረተ ልማት እቅድን ተግባራዊ በማድረግ ተራክተሮቹ ለታለመለት አላማ እንደጠቀሙበት እንድሁም በምግብ ዋስትና ራሳችን እንድንችል የመስረተልማት ሀብቶቻችን በባላቤትነት ስሜት እንድረባረቡ አሳስቧል። በተጨማሪም የዞንና ወረዳ አስተዳደሮቹ የክልሉ የመስረተ ልማት ተኮር እቅድ አስመልኪቶ ለየአከባቢያቸው ማህበረሰብን የተሻለ ግንዛቤ እንድሰጡና ህዝቡን በግብር ስራዎች እንደሰማሩ በማድረግ፤በምግብ  ዋስትና ራሳቸው እንድችሉ ህዝብን የማነቃቃት ስራ መስራት ይጠብቅባቿል ብሏል ቢሮ ሃላፊው።

 ለዞኖችና ወረዳዎች የመጣለት ተራክተሮች 114 ሲሆኑ 80 የሚሆኑ ተራክተሮች የ80 ፈረስ ጉልበት ያለቸው ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ የ40 ፈረስ ጉልበት አላቸው ተብሏል።ከሁለቱም አይነት 46 ለሚሆኑ በዘኖችና ወረዳዎች አመራር ተረክቧል።