የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር አብዲ መሀሙድ በኬንያ ናይሮቢ የሚኖሩ የኢ. ሶ.ክ.ኮሙኒቲ አወያዩ

ናይሮቢ(cakaaranews),እሮብ፤የካቲት 7/2010. የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር  አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በኢትዮጵያ የኬንያ ባላሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሚፍቱ እና ከሌሎችየፈዴራልና ክልል ከፍተኛ  ባላስልጣናት ጋር በመሆን በኬንያ ናይሮቢ የሚኖሩ የኢ. ሶ.ክ.ኮሙኒቲ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አወያዩ።

በምክክር መድረኩ ላይ በክልሉ ባለፎ 8 አመታት የተሰሩ ሁሉም የልማት አውተሮች አጭር ሪፖርት በመፍቻ ንግግራቸው ያቀረቡት የኢ.ሶ.ክ.መ. ፕሬዝዳንት ክቡር  አብዲ መሀሙድ ኡመር በክልሉ እየተከናወኑ ያለው ዘርፈ-ብዙ የልማት፤የጸጥታ፤የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የመልካም አስተዳደር እንድሁም በክልሉ የኢንቬስትመንት ስራዎችን የበኩላቸው ድርሻ እንድወጡና በኬንያ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዲያስፖራ አካላትና አጠቃላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሀገራቸው መጥቶ በሀገሪቱን በክልሉ እየተሰራ ያሉት የልማት ስራዎችን እንድሳተፉ ጥር አቀርቧል።

 

በሌላ በኩል በኬንያ ናይሮቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ዲያስፖራ ኮሙኒቲ አባላት በክልሉ ፕሬዝዳንት የሚመራ የክልሉ ልኳን ቡዱን  መጀመሪያ የክልሉ መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶ.ህ.ዴ.ፓ.በሀገሪቷም ያከናወኑት ዘርፈ-ብዙ የልማት፤የሰላም፤የዴሞክራሲ ስርዓትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በሰፊ ማከናወናቸው በማመስገን፤ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ  አብዲ መሀሙድ ጋር በመወያየታቸው ደስተኛ ከመሆናቸው በዘለለ መድረኩ ታሪካዊ መድረክ መሆኗን ገለጹ።በተጨማሪም ሰመኑን በኬንያ ናይሮቢ ከተማ ኢ.ፈ.ዴ.ሪ.መንግስት ከኦብነግ  ጋር ያደረገው የሰላም ድርድሩ አበራታች ውይይት ነበር ብሏል።ዲያስፖራ አባላቱ ከድርድሩ ድንቅ ውጤት እንመጣ ከመመኘታቸው ባሻገር፤ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል እየተሰራ ያሉት ዘርፈ-ብዙ የልማት፤የሰላምና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን የበኩላቸው ድርሻን በሃላፊነት እንደሚሳተፉም ቃል ገብቷል።