የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ከ1500 ታራሚዎች በይቅርታ ለቋቸዋል

ጅግጅጋ(cakaaranews)እሮብ፤የካቲት የካቲት 14/2010ዓ.ም.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ከ1500 በላይ ታራሚዎች በምህረት ለቋቸዋል።ታራሚዎቸቹ በፀረ-ሰላምና በሌሎች ወንጀሎችም የተፈረዱበት የነበሩ ሲሆኑ የክልሉ ምህረት  ኮሚቴ የታራሚዎቹን ወንጀል በማጣራትና በመለየት በአሁነኑ ወቅት መልቀቅ እንዳለበት ለክልሉ ፕሬዝዳንት ካቀረቡለት ወዲህ ፤ፕሬዝዳንቱ ደግሞ የኮሚተው ውሳኔ በመቀበል ከ1500 በላይ ታራሚዎች ምህረት እንድለቁ አደርጓል።

በሌላ በኩል በፈዴራል ማረሚያ ቤቶች  ያሉት ታራሚዎች  ሁለት አይነት መሆናቸውም ተገልጿል።እነሱም:-

1.  በክልሉ ፍርድቤቶች የተፈደረዱና ለፈዴራል ማረሚያቤት በአደራ መልክ የተሰጡ ሲሆኑ የመልቀቅ ጉዳያቸ ውም በክልሉ ይቅር ኮሚተ የሚወሰን ናቸው 

 2.በፈዴራል ፍርድቤቶች የተፈደረዱና የመልቀቅ ጉዳያቸውም የፈዴራል ምህረት ኮሚቴ የሚወሰን ሲሆኑ፤የክልሉ መንግስት በፈዴራል ማረሚያቤቶች የነበሩ የሌሎች ብሔረሰቦች እስረኞች ስለተፈቱ፤በፈዴራል ማረሚያቤቶች ያሉት የኢትዮጵያ ሶማሌ ታራሚዎችም በምህረት እንደለቁ በአክብሮት ይጠይቃል።

 በተጨማሪም እስረኞችን በምህረት መለቀቅ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የተለመደና የጥንቱ ባህል እንደሆነም አይዘነገም።