በዶሎ አዶ ወረዳ በቡርአሚኖ ቀበሌ ለ1300 ሜትር የሚጓዝ የመስኖ ልማት ከናል ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን ተገለጸ

ዶለውአደው(cakaaranews)ቅዳሜ ፤የካቲት 17፤2010ዓ.ም. የክልሉ ህዝብ ከአርብቶ አደርነትና ከፍል አርሶአደርነት ለማሸጋገር ከሚደረግባቸው ልማታዊ እቅዶች አንዱ በወንዞች  አከባቢ የሚኖሩ የክልሉ ህዝብ በመንደር ማሰባሰብና ተፋሰስ ልማት ፖሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሊባን ዞን፤ በዶሎ አዶ ወረዳ ቡርኣሚኖው ቀበሌ በተፋሰስ ልማት ተጠቃሚ ለሆኑት ከአንድ ሺ አባወራዎች በላይ ኑሮ እንዳሻሽል የታሰበለትና 1300 ሚትር ርዝመት ያለው የመስኖ ልማት ቦይ ግንባታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የዶሎ አዶ ወረዳ ም/አስተዳደሪናየፀጥታና ፊትህ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሀሙድ ሃጂ ገልጿል።

በተጨማሪም በወረዳው የሚኖሩት ህብረተሰብ  ፖሮጀክቱ ለክልሉና ለሀገርም ወሳኝ ጥቅም ያለው መሆኑን አብራርተዋለ።የፖሮጀክቱ ዋና አላማው የሀገሪቱን ህዝብ ከደህነትና ሆላቀሪነት ማላቀቅ እንድሁም የክልሉ መስረተ ልማት ተኮር እቅድ እውን  ለማድረግና ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የሚታደርገው ራኣይ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሆነ ነው የወረዳ ም/አስተዳደሪአቶ ሞሀሙድ ሃጂ  የገለጹት፡፡ አያይዞም የፕሮጀክቱ ግንባታ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ወጣቶችና ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎች የመጡና ከአከባቢው ህዝብ ጋር በሰላም አብሮ የሚኖሩ ወጣቶችም የስራ እድል እንደተፈጠረላቸውና  ተጠቃሚ እንዳደረገባቸውም ሃላፊው ተናግሯል።

 በአጠቃለይ ይህ የመስኖ ልማት ፖሮጀክት ሀገሪቷ ካስቀመጠች የመሰረተ ልማት ፖሊሲዎች አንዱ ከመሆኑ በላይ በቅርቡ በአከባቢው የሚኖሩ ከፍል አርሶአደር ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታመናል።