የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ የዘመናዊ አምቡላንሲ ቁልፍ ተረከበ

አዲስአበባ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤የካቲት 20/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ለዋርዴር አጠላይ ሆስፒታል አገልግሎት ለሚሰጥ የዘመናዊ አምቡላንሲ ቁል ከUNFPA ድርጅት ተረከቧል።

የUNFPA ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቢቲና እና በጀፓን የኢትዮጵያ አምበሲ ተወካይ አቶ አኪራ ዩቺዳ ለኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ አይደሩስ አህመድ የዘመናዊ አምቡላንሲ ቁልፍ አስረክቧል።በተጨማሪም  የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ አይደሩስ አህመድ ለUNFPA ድርጅትና ለጃፓን ኤምበሲ  አመራር የላቀ ምስገና ከማቅረቡ ባሻገር ዘመናዊ አምበላንሱ ለክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላት ሲሆን በተለይ በዋርዴር ወረዳ አከባቢ ለሚኖሩ እናቶችና ህፃናት ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት እንደሰጥ  የታሰበ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም ም/ቢሮ ሃላፊው ከድርጅቱ አመራርና ከጀፓን ኤምቤሲ የስራ ሃላፊዎችጋር በክልሉ ጤና ቢሮ በእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ማሳደግና በጎጂ ልማዳዊ ድርግቶች እንደ የሴት ልጅ ግርዛት መከላከል ዙሪያ ተወያይቷል።በተጨማሪም UNFPA ድርጅት በክልሉ እየሰጡ ላለው የጤና አገልግሎት ሥራዎች እንደሚያስፋፉና በሀገሪቱ ጤና ፖሊሲ መሰረት እንደሚሰሩም ተስማምቷል።