የኢ.ሶ.ክ.መ.ምክርቤት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ ተጀመረ

ጅግጅጋ (Cakaaranews)እሮብ፤የካቲት 21/2010ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት 5ተኛ የስራ ዘመን፤6ተኛው መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ርዕሰመዲና በጅግጅጋ ከተማ በቀርያን ዶዳን አደራሽ ተጀመረ።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የም/ቤቱ አፈጉባኤና የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርት(ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.)ሊቀመንበር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ ኢብራህም  የምክርቤቱ አባላት ከ51% በላይ በመገኘታቸው ካረጋገጡ ወዲህ በ6ተኛው መደበኛ ጉባኤ ከሚገመገሙና ከሚጸድቁ ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል
1. በ5ተኛው የምክርቤቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ የቀረቡት ውሳኔዎች ማፅደቅ
2. የክልሉ መንግስት በ2010ዓ.ም.የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መገምገም

3.የተለያዩ ውሳኔዎችን ማፅደቅ

3.1. የክልሉ የሥራ አመራርና ሲቪል ሴርቪስ ኮሌጅ የተቋቋመበት ደንብ በድጋሜ የተሻሻለበት አዋጅ ማጽደቅ እንደሚገኝበት አፈጉባኤ መሀመድረሺድ ኢሳቅ አክሎ አብራርቷል።

በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.5ተኛው ዘመን ም/ቤት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ዛሬ ካሰዓት በኋላ የክልሉ መንግስት በ2010ዓ.ም.የመጀመሪያ 6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚቀርብና ምክርቤቱ ካዳመጡ በሆላ አቅጣጫ እንደሚያስይዙም አፈጉባኤው ገልጿል።