የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 5ተኛ ዘመን ም/ቤት 6ተኛው መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን መግባቱን ተገለፀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሐሙስ፤የካቲት 22/2010ዓ.ም.በትላንትና እለት በክልሉ ርዕስመዲና በጅግጅጋ ከተማ በቀርያንዶዳን አደራሽ የተጀመረው የኢትዮጵያሶማሌክልል መንግስት 5ተኛየስራዘመን፤6ተኛውመደበኛጉባኤ ሁለተኛ ቀን መቀጠሉን የም/ቤቱ አፈጉባኤ  ገልጿል።

በተጨማሪምበኢ....5ተኛውዘመን/ቤት 6ተኛመደበኛጉባኤላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በክልሉ መንግስት 2010..የመጀመሪያ 6 ወራትእቅድአፈጻጸምሪፖርት አቀርቧል።በተያያዜም ፕሬዝዳንቱ ባለፉት 6 ወራት በክልሉ መንግስት በውሃ ሀብት፤በግብርና ፤በትምህርት ተደራሽነትና ጥራት፤በጤና አገልግሎት አሰጣጥ፤በመንገድ መስረተ ልማት፤በመንደር ማሰባሰብ ፖሮግራሞችና በተፋሰስና መስኖ ልማትና መሰል  ዘርፎች ላይ የተከናወኑት ስራዎች በሰፊው ዳስሷል።

አያይዞም የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ የሆኑት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቆፈራና ጫዋማ ውሃ የማጣራት በኩል የተሰሩት ተግባራት ከመተንተናቸው በዘለለ፤በክልሉ መንግስት በዞኖችና ወረዳዎች ለማስተሳሰር የታቀዱት መንገዶችና ድልድዮች 100% በመቶ በታቀደው መሰረትእንደተሳኩና የክልሉ ህዝብ እለት ተእለት እንቀስቃሴዎች ወሳኝ ሚና ያላቸው ትላልቅ ድልድዮች በክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ላይ መገንባታቸውን ክቡር ርዕሰ መስተዳደሩ አብራርቷል።

በተጨማሪም ም/ቤት አባላቱ በክልሉ መንግስት 2010..የመጀመሪያ 6 ወራትእቅድአፈጻጸም ላይ በቀረበውሪፖርት በመገምገምችና በመወያየት ሪፖርቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።በመጨረሻም የክልሉ /ቤት 6ተኛመደበኛጉባኤለቀጣዩ ቀናት እንደሚካሄድ የም/ቤቱ አፈጉባኤ ገልጿል።