የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ም/ቤት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

 

 

 

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ ፤የካቲት 26/2010ዓ.ም. ባሳለፍ ነው ቀናት በኢ.ሶ.ክ.መ.በጅግጅጋ ከተማ በቀርያንዶዳን አደራሽ ስካሄድ የነበረውን የኢ.ሶ.ክ.መ. ምክርቤት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

በተጨማሪምበኢ....ምክርቤት 6ተኛመደበኛጉባኤላይ የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በክልሉ መንግስት 2010..የመጀመሪያ 6 ወራትእቅድአፈጻጸምሪፖርት  በሰፊው አቅርቧል።በተያያዜም በመንፈቀ አመቱ ላይ የክልሉ መንግስት በውሃ ሀብት፤በመንገዶች መስረተ ልማትና በትላልቅ ድልድዮች ግንባታ  ዘርፎች ላይ የተከናወኑት ስኬቶች በሰፊው ማብራሪያ ከመስጠታቸው ባሻገር የክልሉ አርብቶ አደር ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል የታቀዱት የንጹህ መጠጥ ውሃ እቅዶች አመርቂ ተግባራት መከናወናቸውን ክቡር ፕሬዝዳንቱ አስገንዝቧል።

ባለፈው 6 ወራት በአጠቃላይ የክልሉ ውሃ አገልግሎት ተደራሽነት 66.7% በመነሳት ወደ 73.6% ከማድረሱ በዘለለ የከተሞች ውሃ አገልግሎት በተመለከተ ከ64.5%  በመነሳት ወደ 70.2%ከፍ የተደረገ ሲሆን የገጠር ንጹህ የውሃ አገልግሎት ተደራሽነት ከ66.7% ወደ 73.6% ከፍ ለማድረግ ተችሏል ብሏል ፕሬዝዳንት አብዲ ሞመሀሙድ።በተጨማሪም በክልሉ በርከት ያሉ ትላልቅ ድልድዮች የተገነቡ ሲሆን በትራንስፖርቱ ዘርፍ የታቀዱት ስራዎች ከ100% በታቀዱት መሰረት ተከናውኗል ብሏል ርዕሰመስተዳደሩ።

 

በተጨማሪም የክልሉ ም/ቤት አባላት በክልሉ የስራ አመራርና ሲቪል ሴርቪስ ኮሌጅ የተቋቋመበት አዋጅ ለማሻሻል የቀረበው ረቅቅ አዋጅ ከተወያዩበት በሆላ አዋጁ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።በመጨረሻም  ለአራት ቀናት ያህል በጅግጅጋ ከተማ ሲካሄድ የነበረውን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክርቤት 6ተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቅቋል።