20ኛው አመት የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ምስረተ በዓል በጅግጅጋ ከተማ በአማረና በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሀሙስ፤የካቲት 28/2010ዓ.ም. ይህ የኢትዮጵያ ሶማሊ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.) 20ኛው አመት ምስረተ በዓል በክልሉ ርዕሰመዲና ጅግጅጋ ከተማ በሰይድ መሀመድ አብዲሌ አደራሽ “ህዝባዊነትን መስረት ያደረጉ ድርጅታዊ የሥራ ህደት አላማችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን መሰረት ነው”! በሚል መሪ ቃል  በአማረ መልኩ ተከብሯል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በ2010ዓ.ም. ከወረሃ የካቲት መጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ በሁሉም የኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ከተሞች፤ገጠር አከባቢዎችና ባህር ማዶም ፤በሁሉም የድርጅቱ ደጋፊዎች፤አባላትና በሁሉም የድርጅቱ መካከለኛና ከፍተኛ  አመራሮች  ለኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. 20ኛው አመት ምስረተ በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ መልኩ ሲከናወኑ የነበሩ የፓርቲው 20ኛው አመት ምስረተ በዓል ዝግጅቶች ተጠናቅቆ በዛሬ በየካቲት 28 ቀን ቀንን በክልሉ ዋና ከተማ በጅግጅጋ  በሰይድ መሀመድ አብዲሌ ሀሰን አደራሽ በደመቀት ተከብሯል።በዝክረ በዓሉ ላይም የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር የፓርቲው ሊቀመንበርና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ ጓድ መሀመድረሺድ ኢሳቅ ኢብራህምና የድርጅቱ ም/ሊቀመንበርና የክልሉ መንግስት ርዕሰመስተዳደር ጓድ አቶ አብዲ ሞሀሙድ ኡመርን ጨምሮ የሀገሪቱ ብሔራዊ እህት ስርጅቶች ተወካዮች እንድሁም የክልሉ ም/ፕሬዝዳንቶች፤የድርጅቱና የክልሉ ቀድሞ ሃላፊዎች፤የመንግስት ሰረተኞችና ደጋፊዎች፤የክልሉ ሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ክቡር እንግዶችም ታድመዋል።

 

በፓርቲው 20ኛው አመት ምስረተ በዓል ላይ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድርጅቱ ሊመንበርና የክልሉ አፈጉባኤ ክቡር አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅ  በመጀመሪያ ደጋፊዎችና አባላት በሀገር ውስጥም ሆነ በባህር ማዶም የኢንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው ያስተላለፉ ሲሆን  “ድርጅቱ ባለፈው 10አመታት የፓርቲው ስያሜ ለውጥ ከተደረገ በሆላ በክልሉና ብሎም  በሀገሪቱ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ለውጥ ማምጣት ማስቻሉና  በተለይ በሁለተኛው የክልሉ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራት በታቀዱና በታለሙበት አላማ ለመሳካትና ከዳር ለማድረስ ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. በከፍተኛ ደረጃ እየተረባረበ የሚገኝ ህዝባዊ ፓርቲ ነው” ብሏል። አያይዞም የሀገራችን አንደኛ ዋነኛ ጠላት የሆነው ደህነትን ለማዋጋት የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ በ1ኛ፤2ተኛና 3ኛ ደረጃም ያስቀመጠው ልማታዊ ስተራቴጂዎችና አቅጣጫዎች በክልሉ የሚገኘው የተፈጥሮ የከርሰ ምድርና የምድር ውሃ ሀብታችን አቅማችን በፈቀደው ያህል በአግባቡ መስራትና አርብቶአደሩና ከፍል አርሶአደሩ ህዝብን ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑንም ሊቀመንበሩ አብራርቷል። በተያያዜም  ኢሶህዴፓ ባለፈው አምስተ አመታት  ውስጥ በክልሉ ውሃ ሀብት ዘርፍ በርከት ያሉ ተግራት በማከናወንና የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ በማድረግ አመርቂ ስኬቶችና የህዝቡ ጥያቀ በትክክል የመለሱ ለውጦችን ያስመዘገበ ድርጅት መሆኑንም ሊቀመንበሩ አስረድቷል።በተጨማሪም ጓድ መሀመድረሺድ ኢሳቅ  ኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. በኢኮኖሚያዊ፤ማህበራዊ፤ፖለቲካዊና በመልካም አስተዳደር እንደሁም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መሰረት ያደረጉ የህብረተሰቡ ጥያቄዎችን የሚመለሱበት ፖሊሲዎችና ስተራቴጂዎችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉም ተናግሯል።

በሌላ በኩል በክብረ በዓሉ  ላይ ንግግር ያደረጉት የኢሶህዴፓ ም/ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ጓድ አብዲ መሀሙድ ኡመር በመጀመሪያ መላው የድርጅች አባላትና ደጋፊዎች በአገር ዉስጥም ሆኑ በውጭ  ለ20ኛው ጊዜ የሚከበረውን የድርጅቱ ምስረተበዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው አስተላልፏል። በመቀጠልም ለድርጅቱ መስራች ወጣት ታጋዮች ለድርጅቱ የከፈሉት መጸዋትነት ጀግንነት በተሞላበት መልኩ  ባካሄዱት ትግልን የላቀ ምስጋና አቀረቧል፡፡ ም/ሊቀመንበሩ ዓሉን አስመልክቶ በላፉት 20 አመታት ድርጅቱ ያሳለፈው የትግል ዘመን ያጋጠሙት መስናክሎችና ፈታኝ ተግባራት እንዲሁም በፓርቲው ትግል ለመሳካት የተጠቀሙት ድርጅታዊና ታሪካዊ ሰልቶች ለሚዘከሩ መሆናቸውና በድርጅቱ ታሪክ መዝገብ መካተት ያለባቸው ጠንካራ ስትራቴጅዎች እንደሆኑም አብራርቷል።አያይዞም ለወደፊት የድርጅቱ ተተኪ አመራር ልምድና ትምህርት የሚቀሰሙበት ስለሆኑ የክልሉና የድርጅቱ አባል ወጣቶች በእንዲህ አይነት ድርጅታዊ መድረኮች ለተሞክሮ ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑንም ክቡር አብዲ መሀሙድ አስታወቋል።በመሆኑም አሁን ድርጅቱ የደረስንበት የሰላም፤ የልማትና የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ለማስፈንና የድርጅቱ አማላዎች ለማሳካት የተደረጉ ጥረቶች  ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች እንደ ነበሩና ሁላችንም የከፈልነበት ታሪካዊ መፀዋትነት ዉጤት እንደሆኑ ከመግለጻቸው ባሻገር ለወደፊትም የክልላችን ህዝብ ለዘመናት ስያሰቃይ ነበረውን የደህነት ተራራዎች ለማፍረስ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎችን ትልቅ ሥራ  መስራት ይጠብቅብናል ብሏል  የፓርቲው ም/ሊቀመንበር።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል “ከ10አመታት በፊት ሰላም የቀራው፤ልማት የናፈቀውና በሙስና አሰራር ምንም ለውጥ ሳያሳይ በስም ብቻ ያለ ክልል እንደነበረ ነው ያነሱት የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. ም/ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ሲሆኑ የቀድሞ የመሪ ድርጅቱን ስያሜ(ሶህዴፓ) መቀየር ያስፈለገበትም ምክንያት በተለያዩ ሀገራት ከሚኖሩ የሶማሌ ድርጅቶችና ብሔረሰብን ለመለየትና ራስን በሚገባ ተገንዝቦ እና ለይቶ የልማት ፖሊሲዎችና አቅጣጫዎችን ለመንደፍ ሲባል ነው” ብሏል።በተያያዜም የኢሶህዴፓ ባለፉት 20 አመታት በተለይም ድርጅቱ የስምና የአርማ እንድሁም አጠቃላይ የክልሉ ስም ለውጥ አደርጎ ከተንቀሳቀሰበት ወቅት ጀምሮ የክልሉ ህብረተሰብ አሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ የታዩ ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች በክልሉ ህዝብና በውጭ አገራት የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች የበለጠ ኢትዮጵያዊነት ስሜት ያሳደሩት ለውጦች ተጠናክሮ እንድቀጥሉ ክቡር ፕሬዝዳንቱ የገለፁ ሲሆን በጅግጅጋ ከተማ የተከበረው የኢ.ሶህ.ዴ.ፓ.20ኛ አመት ምስረተ በዓል በቀጣይ በክልል ደረጃ በድምቀት ተባብሮ እንደሚውልም አስታውቋል።

በሌላ በኩልም የቀድሞ የድርጅቱ አመራሮችና የክልል ርዕስተዳደሮች የነበሩት ነባር ታጋዮች ክልሉ በእነሱ ወቅት የነበው ስርዓትና የክልሉ እድገት ደረጃ ኣና በአሁኑ የተመዘገቡት ዘርፈ ብዙ የሰላም ፤ የመስረተ ልማትና የመልካም አስተዳደር ድሎች ትልቅ ለውጥ እንደለ አስመስክረዋል፡፡በተያያዜም በ20ኛው የኢ.ሶህ.ዴ.ፓ.ምስረተ በዓል መድረክ በክቡር እንግዳነት የተጋበዙና የተሳተፉ  የቀድሞ የድርጅቱ ሊቃነ መናብርትና በተለያየ ወቅቶች የክልሉ ርዕሳን መስተዳደሮች  የነበሩት ነባር ታጋዮች አዲሱ የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ. አመራሮች በክልሉ ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች በማስመዝገባቸውና የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፁ፤የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች  ክልሉ በአሁኑ ወቅት የደረሰበት ዘርፈ ብዙ የእድገት ዉጤቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ መዘንጋት እንደሌለባቸውና ድርጅቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጀመው የለውጥ ትግሉን እንዲቀጥሉበት በማሳሰብ የአባትነት ምክር መልዕክታቸውን አስተላልፏል፡፡  

በመጨረሻም ባለፉት 20 አመታት በድርጅቱ የልማት ትግል ጊዜያት እንደ ትልቅ መሣሪያ ሆኖ በወቅቱ የነበሩት ፈታኝ ሥራዎች ለማሸነፍ በአርቲና ጥበብ ካገዙት የክነጥበብ ቡዱኖች በማወዳደር በ20ኛው የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ምስረተ በዓል መድረኩ ላይ ለአሸናፊዎችን የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቿል። የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.20ኛው አመት ምስረተ በዓል ሥነስርዓትም “ህዝባዊነትን መስረት ያደረጉ ድርጅታዊ የሥራ ህደት አላማችን ለአንድነታችንና ለህዳሴያችን መሰረት ነው! የሚል መፈክር ተደምድሟል።