በሸቤሌ ዞን ቀላፎ ወረዳ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገናና ህኪምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ቀላፎ(Cakaaranews) ሰኞ፤መጋቢት4፤2010ዓ.ም.በመቶዎች ለሚቆጠሩ አይነ ብርሃናቸው የአይኖ ሞራ የተጋረዱ ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርገው ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱን በሸቤሌ ዞን ቀላፎ ወረዳ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራም በአጠቃላይ በኢ.ሶ.ክ.መ.አከባቢዎች የሚኖሩና አይናቸውን በአይን ሞራ የተጋረዱ እንድሁም በሌሎች ችግሮች አይነ ብርሃናቸው ላጡ ሶዎች ተጠቃሚ ያደረገና የበርካታ ዜጎች አይነ ብርሃን ያስመለሰ ፖሮግራም ሲሆን ለአንድ ሳምንት ሳምንት በቀላፎ ወረዳ ለሚኖሩና የማየት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች ትክረት አደርጎ በመቶዎች የሚቆጠሩ  ዞጎች በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቀው የወረዳው ጤና ቢሮ አስታውቋል።በተጨማሪም የኢ.ሶ.ክ.መ.ተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱኑ ባለፎ ሳምንት በኤረር ዞን ፊቅ ወረዳ ሲያካሄዱ የነበረውን ነጻ የአይን ቀዶ ጥገናና ህኪምና አገልግሎት  ማጠናቀቃቸውን ገልጿል።

በተያያዜም በቀላፎ ወረዳ አከባቢዎች የሚኖሩና አይነብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች ፖሮግራሙ  በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢ.ሶ.ክ.መ. ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠቱን አመስግኗል።በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ቡዱኑ በቀላፎ ወረዳ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደምቆዩ አብራርተዋ።

ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሚሰራ ልዩና ብቸኛ ፖሮግራም ሲሆን የክልሉ ህዝብ ተጠቃሚ ያደረገ የጤና አገልግሎት  ሰጭ ፖሮግራም ነው።