የኢ.ሶ.ክ.መ.ውሃ ሀብት ቢሮ ሃላፊ በክልሉ ውሃ አገልግሎት ተደራሽነት ዙሪያ ሪፖርት አቀረቡ

ጅግጅጋ(cakaaranews)አርቢ፤መጋቢት 5/2010ዓ.ም.የኢ.ሶ.ክ.መ.ውሃ ሀብት ልማት ቢሮና የኢ.ሶ.ህ.ዴ.ፓ.ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፈርቱን አብዲ ማህዲ በጽ/ቤቷ ለክልሉ ሚዲያ አውተሮች ባለፈው 10 አመታት የክልሉ መንግስት በውሃ ሀብት ተደራሽነት ያስመዘገበው ለውጦችና በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተሰራ ያለው የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች በደረሱበት ደረጃ አስመልኪቶ ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ከ10 አመታት በፊት በአጠቃላይ በክልሉ የነበረውን የውሃ ተደራኝነት ችግሮች በማስታወስ፤በአሁኑ ወቅት በከተሞች ውሃ አገልግሎትና የውሃ ልማት ዝርጋታና ተጠቃሚነትን በተመለከተ የክልሉ መንግስት በርካታ ስኬቶች ማስመዝገቡና በከተሞች የሚኖሩ የክልሉ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ማድረግን ቢሮ ሃላፊው ገልጿል።በተያያዜም በቅርብ ርቀት የማይገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚገኘው ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚና ተደራሽ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች አበረታች ውጤቶት ማስመዝገብን ሃላፏ ገልጿል።

በሌላ በኩል በቅርብ ርቀት የማይገኙ አከባቢዎችና በቅርበት ውሃ የማይገኙባቸው አከባቢዎች ማለትም በሀጉጋ ሜዳ እስከ ጋሻሞ  እየተሰራ ባሉት የንጹህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቶች በአከባቢው ለሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እንደ ኤልበሃይ፤ቃይደርለቢሌ፤ካም ኡመር፤አኔመዶቤ፤ጋሻሞ፤ደጋህዮ አዴና አሊ ጃመዓ የሚኖሩ 78500  ሶዎችና 173,500 እንስሳትም ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑ በዘለል በፖሮጀክቶቹ ግንባታ  216 ሚልዮን ብር የወጣበት ሲሆን ፖሮጀክቱ ለ120ኪ.ሜ.የሚያቋረጥ መሆኑንም ወ/ሮ ፈርቱን አብራርታለች።

በተጨማሪም በኢቲሻለ፤ደደመበኔ፤ኦበሻ እስከ ፊቅ በሁለት ፌስ የሚገነባ የውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክት በኢቲሻለ-ኦበሻ  አንደኛ ፌስ ብቻ በኢቲሻለ፤ቢቃ፤ሀሎቢዬ ደደበኔደዋረቶ፤አሊ ኢትዮጵያና ኦበሻ ቀበሌዎች የሚገኙ አርብቶአደርና ከፍል አርብቶ አርሶአደር ማህበረሰብን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ የሚያደርግ ከመሆኑ ባሻገር ፖሮጀክቱ በ156 ሚልዮን ብር የሚገነባና  19151 ሶዎችና 350 ሺ እንስሳትም የንጹህ መጠጥ ውሃ  ተጠቃሚ ያደርጋል ብሏል።የንጹህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፖሮጀክቱ እስከ 150 ኪ.ሜ.እንደሚዘልቅም ቢሮ ሃላፊው አስረድቷል።