በሊባን ዞን ፊልቱና ዴካ ሱፍቱ ወረዳዎች የሚኖሩ ህብረተሰብ በተዘዋወሪ ጤና አገልግሎት ሰጭ መኪና ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ

ሀየሱፍት( cakaaranews)እሁድ፤መጋቢት 9/2010ዓ.ም.በባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስከናወኑባቸው ከነበሩ የልማት ስራዎች አንዱ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና የ ክልሉ ህዝቡ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ሲሆን የክልሉ አርብቶ አደርና ከፍል አርሶአደር ማህበረሰብ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት በማዳረስ አመርቂ ተግባራት ተከናውኗል፡፡ የኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የተቀመጠለት እቅዶችና አቅጣጨዎች አንዱ በክልሉ የሚገኙት ጤና ማዕከላት ከጤና ኬላ እስከ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ድረስ በአገልግሎትም ሆነ በሌላም ትስስር እንድኖራቸውና ለህዝቡ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ፡፡

በዚህም በክልሉ ባጄት ከውጭ ሀገር የተገዛና በዘመናዊ መልኩ  የተገጣጠመ ተዘዋዋሪ የጤና አገልግሎት ሰጪ መኪና በፊልቱና ዴካሱፍቱ ወረዳዎች ስር ከሚገኙ የሀዬ፤ሶራና ሀሙር  ቀበሌዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቤት ወደ ቤት ቀልጣፋ የህኪምና አገልግሎት በማዳረስ ላይ ይገኛል።የአከባቢው ማህበረሰብም ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኙት የህኪምና አገልግሎቱ አበረታች መሆኑን ገልጿል።

ይህ ተንቀሳቃሽ የህኪምና አገልግሎት ሰጭ መኪና የተለያዩ የህኪምና አገልጋሎትን ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውር ሲሆን ተንቀሳቃሽ መኪናው ከሚሰጠው አገልግሎት መካከል፤የህጻናት ክትባት፤የእናቶችና ህጻናት እንከብካቤ፤የልጆ ች አልሚ የምግብ አይነቶችና የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ለገጠሩና ለከተሞች ማህበረሰብም እንደሚሰጥ የሀየሱፍቱ ቀበሌ ጤና ጣቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ነጅማ አብዱረሺድ አስረድቷል።

በተጨማሪም ይህ ተንቀሳቃሽ የህኪምና አገልግሎት ሰጭ መኪናው በውስጡ በርካታ የህኪምና መሳሪያዎች የተገጠሙ፤ሁሉም አስፈላጊ የጤና ቁሳቁሶችና ሰው ሃይልም የተሞላለት እእንድሁም በሶለር የሚሰራ፤በገጠራማና የጤና አገልግሎት ሺፋን ቅርበት የማያገኙ አከባቢዎች ለሚኖሩ ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚያዳረስ መሆኑን የሊባንና ዳዋ ዞኖች የሪፍቱ ፖሮግራም አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሁሴን ገልጿል።

በተያያዜም ይህ  ተዘዋዋሪ የጤና አገልግሎት ሰጪ መኪና በክልሉ ገጠራማ አከባቢዎች ለሚኖሩ ማህበረሰብ ያጋጠሙ የነበረውን የጤና አገልግሎት ችግሮ ችን በከፍተኛ ደረጃ የቀረፈ ሲሆን ለገጠሩ ህዝባችን አመርቂ የጤና ሽፋን እያዳረሰ መሆኑን አይዘነገም።