የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በቅርቡ በምህረት የለቀቃቸው ሞዴል ታራሚዎች የዘመናዊ መኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤መጋቢት 10/2010ዓ.ም.በተለያዩ ወንጀሎች ፈጽሞ በተለያዩ የክልሉ ማረሚያቤቶች ታስሮ የነበሩና በቅርቡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት በምህረት ከተለቀቃቸው ታራሚዎች መካከል በእርምት ወቅታቸው ሞዴል የሆኑት ታራሚ ግለሰቦች የክልሉ መንግስት የዘመናዊ መኖሪያቤቶች  ቁልፍ አስረክቧል።

በተጨማሪም ታራሚዎቹ በክልሉ መንግስት በምህረት ከተለቀቃቸው በኋላ በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆችና ማሰልጠኛ ማዕከላት  በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሲወስዱ የነበረው የትምህርትና አቅም ግንባታ ስልጠናቸውን ካገባደዱ በሆላ ታራምዎቹ ከመደበኛ ማህበረሰብ ጋር ለማቀላቀልና ከመንግስት ብቻ ስራ ጠባቂ ሳይሆን ራሳቸው ስራ ፈጣሪ ለማድረግ በትላንትና እለት የክልሉ ልዩ ፖሊስ ዋና አዛዠና የጸጥታና ፍትህ አስተዳደር ቢሮ ተጠባባቂ ሃላፊ ጀኔራል አብዱራህማን አብዱላሂ ቡራሌ እና  የጅግጅጋ ከተማ ካንቲባ አቶ ኢብራህም መሀሙድ ሙባሪክ  በክልሉ መንግስት በዘመናዊ መልኪ የተሰሩ የመኖሪያቤቶች ቁልፍ አስረክቧል።

ታራምዎቹ በበኩላቸው በማረሚያቤቶች የነበሩ ወቅት የክልሉ መንግስት ስብኢና በተሞለ መልኩ ያደረገላቸው እንከብካቤና በቅርቡ ደግሞ የእርምት ጊዜያቸውን ሳያጠናቀቁ በምህረት መለቀቃቸው እንድሁም በምህረት ከተለቀቁ በሆላም የአቅም ግንባታና ግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልጠናዎች ሰጥቶ አሁንም በዘመናዊ መልኪ የተሰሩ መኖሪያቤቶች በመስጠታቸው ደስተኛ ከመሆናቸው ባሻገር ለክልሉ መንግስት የላቀ ምስገናቸውን አቀርቧል።