በደቡብ ጅግጅጋ ወረዳ የሃደው ቀበሌ ት/ቤት ተማሪዎች በአለም የባህላዊ ምግብ አሰራር ውድድር 1ኛ ደረጃ ወጡ

ሃደው(cakaaranews)አርቢ ፤መጋቢት 14/2010ዓ.ም.የሃደው ቀበለ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ 229 የምገባ ፖሮግራም የሚከናወኑባቸው ት/ቤቶች አንዱ ሲሆን በአለማቀፍ የባህላዊ ምግብ አሰራር ከ100 ሀገራት ትምህርትቤቶች ለተወጣጡ ተማሪዎች በሀገራችን ኢትዮጵያ ት/ቤቶች ወክሎ በ “ሹሮ” የተባለ የሶማሌ ባህላዊ ምግብ አሰራር የተወዳደሩ የሃደው ቀበለ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በአለማቀፉ ውድድር ላይ 1ኛ ደረጃ ማውጣታቸውን ተገለጸ።

በተጨማሪም ይህ የአለም ት/ቶች ባህላዊ ምግብ አሰራር ውድድር በኢትዮጵያ ባህላዊ ምግብ የሚወዳደሩ ት/ቤቶች ባሉበት ቦታ ሄዶ ክትትልና ድጋፍ የሚሰጡ ኮሚቴዎች እንደነበሩና በኮሚቴው ግምገማ መሰረት በ “ሹሮ” የሶማሌ ባህላዊ ምግብ አሰራር የተወዳደሩ የሃደው ት/ቤት ተማሪዎች በአለማቀፉ ውድድር 1ኛ ደረጃ ማውጣታቸውን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በተያያዜም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊና በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፖሮግራም የት/ቤቶች ምገባ ፖሮግራም ዋና አስተባባሪ ለውድድሩ የተሳተፉ የሃደው ቀበለ ት/ቤት ተማሪዎች የሽልማትና እውቅና ሴርትፍኬት አበርክቶላቿል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ መሀሙድ አህመድ ኑር የሃደው ት/ቤት ተማሪዎች በሶማሌ ባህላዊ ምግብ አሰራር  በ “ሹሮ”  በአለማቀፉ ውድድር 1ኛ ደረጃ በማውጣታቸው እጅግ ደስተኛና ኩራት ከመሰማታቸው ባሻገር በኢ.ሶ.ክ.መ.የሚገኙና የምገባ ፖሮግራም ተጠቃሚ የሆኑት ት/ቤቶች ትልቅ ለውጥ ያመጣ ፖሮግራም መሆኑንና ከአሁን በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ሲያቋረጡ የነበሩ ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰ አልያም ያጠፋ ፖሮግራም ነው ብሏል።

 በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፖሮግራም(WFP) የት/ቤቶች ምገባ ፖሮግራም ዋና አስተባባሪ ወ/ሮ አስካለች ታግሉ በበኩላ የሀገራችን ት/ቤት ተማሪዎች በሀገራችን ባህላዊ ግምብ አሰራር ተወዳድሮ ከ100 አገራት ት/ቤቶች ለተወጣጡ ተወዳዳሪዎች በማሸነፋቸውና የሽልማትና እውቅና  ሴርትፍኬት ማገኘታቸውን በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

በውድድሩ አሸናፊ የሆኑት የሃደው ቀበሌ ት/ቤት ተማሪዎች በበኩላቸው በአለማቀፍ የባህላዊ ምግብ አሰራር ውድድርን 1ኛ ደረጃ በማውጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ለክልሉ ሚዲያ ገልጿል።

የት/ቤቶች ምግባ ፖሮግራሙ ከአሜሪካ ግብርና ሚንስትር የተገኘ ፈንድ ከመሆኑ በዘለል በ40 የሀገራችን ወረዳዎች የሚገኙ ት/ቤቶች የሚተገበር ፖሮግራም ሲሆን በሀገሪቱ ትምህርት ጥራት፤የተማሪዎች ትምህርት ቀጣይነትና ክትትልን በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለ ፖሮግራም መሆኑንም የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስረድቷል።