በኢ.ሶ.ክ.የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰረተኞች ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉለት

ጅግጅጋ(cakaaranews)ሰኞ፤መጋቢት 17/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰረተኞች ከወር ደሞዛቸው ያዋጡት ድጋፍ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች የምግብና የቤት ቁሳቁስ ዲጋፍ አደረጉለት፡፡

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ሰረተኞች ከወር ደሞዛቸው ባዋጡት ድጋፍ በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች አዋሳን ግጭት ሳቢያ ከኦሮሚያ ክልል ከቤት ንብረታቸውን የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች የምግብና የቤት ቁሳቁስ ዲጋፍ አበረክቶላቿል፡፡

ድጋፉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰረተኞች የተረከቡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቀዮች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሲሆን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሰረተኞች  የላቀ ምስገናቸው አቀርቧል፡፡ የኮሚቴው አባልና የክልሉ ሀገር ሽማግሌ ገራድ ኩላሚዬ ገራድ መሀሙድ ገራድ ዶል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ሰረተኞች ለኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቃዮች ያደረጉለት የሚግብና የቤት ቁሳቁስ እርዳታ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወሳኝ ከመሆኑ በዘለለ ለሌሎችም ተምሳሌት የሚሆን ታላቅ እርምጃ ሲሆን ድጋፉ በክልሉ የሚገኙ የተፈናቃዮች መጠሊያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎቻችን በማድረስ፤ችግሮች ለመፍታትም ትልቅ አካል  ነው ብላል ገራዱ፡፡  

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ፤ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ተወላጆች  ያደረጉለት ዲጋፍ የመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን ፤ ከአሁን በፊትም ቆለቺ  መጠሊያ ጣቢያ ዉስጥ የሚገኙት ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ማህበረሰብ 5ሚልዮን ብር ዲጋፍ ማድረጋቸውን የሚታወስ ሲሆን የባንኩ ሰረተኞች ባሳዩት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ለሌሎች የክልሉ ሰረተኞች ጥሩ ተመክሮ እንደሆነም የኢትዮጵያ ሶማሌ ተፈናቀዮች ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት አስገንዝቧል፡፡