በአውስትራሊያ የሚኖሩ የኦ.ሶ.ክ ተወላጆች 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓልን አስመልክቶ በደማቅ ስነ-ስርዓት አክብሯል፡፡

ሜልቦርን,(cakaaranews)እሁድ , መጋቢት 23, 2010. በአውስትራሊያ የሚኖሩት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጆች 20ኛው የኢሶህዴፓ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በደማቅ ስነ-ስርዓት በሜልበርን ከተማ አክብሯል፡፡  

በዚሁ መሰረት በርካታ የክልሉ ተወላጆች ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተወጣጡና የዲያስፖራው ኮሚኒቲ አመራር አካለት በተገኙበት እንዲሁም የኢ.ሶ.ክ.መ የዲያስፖራ መስተባበርያ ቢሮ ሀላፊና የፕሬዝዳንቱ የህዝብ ቅሬታ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ አብዲረዛቅ ሰሀኔ የቀጥታ ስልክ ተሳትፎ በማድረግ 20ኛው የኢሶህዴፓ ምስረታ በዓልን አስመልክቶ በተለያዩ ሙዚቃዎችና የባህል ዘፈኖችን  በማጀብ በደመቀ ሁኔታ አክብሯል፡፡  የክልሉ መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገባቸውን ውጤቶች ማለትም በኢኮኖሚያዊ፤ በማህበራዊ፤ በፖለትካዊና በፍትህ ፤ዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶችን እንዲሁም በውጭም በሀገር ውስጥም የህዝብ ለህዝብ ትስስር ስራ ተጨባጭና አመርቂ ስኬቶች መሰራቱን ክቡር አቶ አብዲረዛቅ ሰሀኔ በስልክ መብራርያ እንዳደረጉላቸው በአውስትራሊያ የኢ.ሶ.ክ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዲቀኒ ፋረህ ለክልሉ የሚዲያ አውተሮች ተናግረዋል፡፡

አያይዞም አቶ አብዲቀኒ ፋረህ በአውስትራሊያ የሚኖሩት የኢ.ሶ.ክ ተወላጆችና በተቀሩት የአለም ሀገራት ያሉት የክልሉ ተወላጆች ለክልሉ መንግስት እያበረከቱት ያለዉን አስተዋፃና ከኢሶህዴፓ ድርጅት ጎን ቆመው እየሳዩት ያለዉን የበኩላቸዉን ሚና የኢ.ሶ.ክ.መ የዲያስፖራ መስተባበርያ ቢሮ ሀላፊና የፕሬዝዳንቱ የህዝብ ቅሬታ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ አብዲረዛቅ ሰሀኔ ላቅ ያለ ምስጋነ ማቅረቡን  ኣክሎ ገልፀዋል፡፡

 በመጨረሻም በአለም ሀገራት ያሉት የኢ.ሶ.ክ የዲያስፖራ ኮሚኒቲ አካለት ለክልሉ መንግስትና ለኢሶህዴፓ ድርጅት ያለቸዉን ቁርጠኛ ድጋፈቸዉን በማሰየት ለይ መሆናቸዉንና የበኩላቸዉን ሚና በመወጣት ለይ እንደሚገኙ ተገልፀዋል፡፡