እንኳን ደስላቹ እንኳን ደሳለን የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ የፈዴራል የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሠጡ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሀሙስ፤ግንቦት 2 ቀን 2010.የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ከፈተኛ አመራር አካላት የኢሶክመ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድና የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ መሀመድረሺድ ኢሳቅን ጨምሮ በዛሬ እለት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይአህመድ በፈዴራል መንግስት መዋቅር ለሾሙት የኢሶህዴፓ አባላት የእንኳን ደስላቹ እንኳን ደሳለን መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።በዚህም በዛሬ እለት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለፈዴራል  የስራ ሃላፊዎች ከሾሙት መካከል ወ/ሮ ሰሀርላ አብዱላሂ የኢፌዴሪ የህዝብተወካዮች ም/ቤት አባልና በጤና ዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ያላት ሲትሆን የኢፈዴሪ ጤና ጥበቃ ሚንስተር ዴታ ተደርጋ ተሾመዋል።በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትር ሚንስቴር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚንስተር ዴታ የነበችው ወ/ሮ ፈርሂያ መሀመድ የኢፈዴሪ ወጣቶችና ስፖርት ሚንስቴሪ ሚንስተር ዴታ የተደረገች ሲሆን ወ/ሮ ኢፍራህ አሊ ሙሳ በነበረችው የሳይንስና ቴክኖለጂ ሚንስተር ዴታ በድጋሜ ተሾመዋል።

 በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት ለተሾሙት አዳዲስ ሚንስቴር ዴታዎች በገሀሪቱ አመራርነት ከፍተኛ ለውጥ እንዲያስገኙ ዘንድ የተመኘ ሲሆን የኢ.ሶ.ክ.መ.መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ ለኢህአዴግ ማዕካለዊ ጽ/ቤትና ለኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ስም ዝርዝራቸው መላኩን ይታወሳል።

 በመጨራሻም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስትና የክልሉ መሪ ድርጅት ኢሶህዴፓ አመራር አካላት የኢሶክመ.ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመርን ጨምሮ ለኢህአዴግና ለኢፌደሪ ጠቅላይ ሚንትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢሶህዴፓ ጥያቀ በአግባቡ በመመለሳቸውን የላቀ ምስገና ያቀርበዋል።

 

ለተሾሙት አዳዲስ ሚንስቴር ዴታዎችን የክልሉ መሪ ድርጅት ለኢሶህዴፓ ከፍ ያለ ምስገና ያቀርበዋል።