የኢ.ሶ.ህ.መ.ተንቀሳቃሽ የአይን ሃኪሞች ቡድን ለቦኽ ወረዳ ማህበረሰብ የአይን ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተገለጸ

ቦኽ(cakaaranews)እሁድ፤ግንቦት 05/2010ዓ.ም.በመቶዎች ለሚቆጠሩ አይነ ብርሃናቸው የአይኖ ሞራ የተጋረዱ ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርገው ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱን በዶሎ ዞን ቦህ ወረዳ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

በተያያዜም በቦህ ወረዳ አከባቢዎች የሚኖሩና አይነ-ብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች ፖሮግራሙ  በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ነጻና ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠታቸውን አመስግኗል።በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ሃኪሞች ቡዱኑ በዶሎ ዞን ቦኽ ወረዳ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደምቆዩና ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንደሚሰጡም ገልጸዋል።

በተያያዜም በቦኽ ወረዳ አከባቢዎች የሚኖሩና አይነብርሃናቸው በተንቀሳቃሽ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች የተመለሰላቸውን ነዋሪዎች ፖሮግራሙ  በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ከመሆኑ በሻገር የኢ.ሶ.ክ.መ. ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪሞች መድቦ በነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና አገልግሎት መስጠቱን አመስግኗል።በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ  የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ቡዱኑ በቦኽ ወረዳ ለአንድ ሳምንት ያህል እንደምቆዩ አብራርተዋ።

ተንቀሳቃሽ ነጻ የአይን ቀዶ ጥገና ህኪምና ፖሮግራሙ  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የሚሰራ ልዩና ብቸኛ ፖሮግራም ሲሆን በአይነ-ብርሃናቸው የአይን ሞራና ሌሎች በሽታዎች ተጋርዶ የነበሩ በርካታ የክልሉ ህዝብ አይንብርሃናቸው ያስመለሰላቸውና ተጠቃሚ ያደረገ የጤና አገልግሎት  ሰጭ ፖሮግራም ነው።